Site icon ETHIO12.COM

የሶማሌ ክልል ካቢኔ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር እንዲገቡ የቀረበውን ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ደገፈ

የሶማሌ ክልል ካቢኔ ዛሬ በደረገው ስብሰባ ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ ለማድረግ የተወሰነው የውሳኔ ዕቅድ በሙሉ ድምጽ መደገፉን ክልሉ በይፋዊ የትሥር ገጹ ይፋ አደረገ።

ካቢኔው የሶማሌ ክልሉ ልዩ ኃይል ኢትዮጵያ አስቸጋሪ ፈተና በገጠማት ጊዜ ሕይወታቸውን ሠውተዋል። በክልላቸው መንግስት የተሰጣቸው ግዳጆችን በጀግንነት በመወጣት የሃገራችንን ዳር ድንበር አስከብረዋል ያለ ሲሆን የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ለሀገራችው የሚችሉትን ሁሉ ያደረጉ፤ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጀግንነት የተወጡ፤ ለወደፊትም በተሻለና ይበልጥ ኢትዮጵያን ማገልገል በሚያስችላቸው ቦታዎች ላይ እንደ የፍላጎታቸው ተመድበው እንዲያገለግሉ የተወሰነው ውሳኔ የክልሉ መንግስት በመደገፍ አስፈላጊ የሆነውን ሙሉ ደጋፍ ይሰጣል ብሏል።

በዚህም መሰረ ካቢኔው ተከታዮቹን ውሳኔዎች አሳልፏል።

የክልል የጸጥታ ሃላፊዎችና አመራሮች ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ መስማማታቸውን ከትናንት በስቲያ ባሳለፉት አቋም ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

Exit mobile version