Site icon ETHIO12.COM

በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል

እራሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባል እንደሆነ በማስመሰልና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አራራት ሆቴል አካባቢ ያለው አምስት ሺህ ካሬ ሜትር ባዶ ቦታ በከተማው ካቢኔ በምደባ አስወስንልሀለሁ በማለት የማታለል ወንጀል የፈጸመው አቶ ፍቅረስላሴ ታደሰ እና ግብራአበሮቹ በቁጥጥር ስል ውለዋል።

ግለሰቡ ሰላሳ ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ትከፍላለህ ብሎ በማሳመን የግል ተበዳይ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዳያድርበት ለማድረግ በተለያየ ጊዜ የተፈረሙ ሰነድ በማስመሰል እና ራሱን የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና የመልካም አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ በማድረግ ሀሰተኛ ቲተርና ክብ ማህተሞችን በማዘጋጀት የተለያዩ ደብዳቤዎች ላይ በመፈረም ደብዳቤዎች ለግል ተበዳዩ በማሳየት የማሳመን ስራ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

1ኛ ተጠርጣሪ የግል ተበዳይ አቶ ፍቅሬ በየነ የተባሉትን መሬት መግዛት እንደሚፈልግ ካረጋገጠ በኋላ እራሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባል እንደሆነ እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አራራት ሆቴል አካባቢ ያለው አምስት ሺህ ካሬ ሜትር ባዶ ቦታ በከተማው ካቢኔ በምደባ አስወስንልሀለሁ በማለት ሰላሳ ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ትከፍላለህ ብሎ በማሳመን የግል ተበዳይ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዳያድርበት ለማድረግ በተለያየ ጊዜ ካቢኔዎች የፈረሙበት ሰነድ በማስመሰል እና ራሱን የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና የመልካም አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ በማድረግ ሀሰተኛ ቲተር እና ክብ ማህተቦችን በማዘጋጀት የተለያዩ ደብዳቤዎች ላይ በመፈረም፤ ደብዳቤዎቹን ለግል ተበዳዩ በማሳየት፤

2ኛ ተጠርጣሪ ታምራት እስጢፋኖስ ወደ ሚሰራበት ቢሮ ይዞት በመሄድ ከሁለተኛ ተጠርጣሪ ጋር በማስተዋወቅ ሁለተኛ ተጠርጣሪም በሀሳቡ ሙሉ በሙሉ በመስማማት የግል ተበዳይን ጉዳዩ ቀላል እንደሆነና በቀላሉ ሊያስወስኑለት እንደሚችሉ በማሳመን የግል ተበዳይን የተለያዩ ሰነዶች እንዲያቀርብ ካደረገ በኋላ 1ኛ ተጠርጣሪ ፍቅረስላሴ ታደሰ የበለጠ የግል ተበዳዩ ላይ እምነት እንዲያድርበት በማሰብ ወደ 3ኛ ተጠርጣሪ ዘውዱ ደገፋ የተባለው ግለሰብ ወደ ሚሰራበት የካ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ በማገናፕት

3ኛ ተጠርጣሪም በተመሳሳይ በጉዳዩ በመስማማት ቦታው ድረስ ሂዳ ልኬት እንድትፈጽም 4ኛ ተጠርጣሪ የሆነችውን ቃልኪዳን አክሊሉ የተባለቸዋን መሀንዲስ በመመደብ እና ልኬት እንዲወሰድ በማድረግ ጉዳዩን በቀላሉ ማስወሰን እንደሚችሉ በቀጥታ ለግል ተበዳይ በመናገር ከፍተኛ እምነት እንዲያድርባቸው ያደረጉ ሲሆን 1ኛ ተጠርጣሪ በስምምነታቸው መሰረት በተለያየ ቀን የ8,250,000/ ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ ብር/ ቼክ በመቀበል ተጠርጣሪዎች በጋራ በመሆን ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ምክንያት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

Ena

Exit mobile version