Site icon ETHIO12.COM

ላም ሲሳይ ይዛ መጣች!

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ ደዋሮ ቀበሌ ልዩ ስሟ «አካሌ ባድማ» በተባለች መንደር ልጃቸውን ለመዳር በ18 ሺህ ብር  የገዟት ላም 40ሺህ ብር የሚጠጋ ዋጋ ያለው ማዕድን ለባለ ሰርጎቹ አበርክታለች።

በበህር ዳር ከተማ የጋፋት ወርቅ ቤት ባለቤት አለልኝ ማተቤ ማዕድኑ በተለምዶ ወርቅ ይባል እንጂ ወርቅ አይደለም፣ ዋጋው ግን ከወርቅ ማዕድን በእጅጉ ከፍ ያለ እንደሆነና በዋናነትም ጃፓነችና ቻይናዎች እንደሚገዙት ለዶይቼ ቨሌ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ማሞ በበኩላቸው በአንዳንድ የቆላማ አካባቢዎች በሚገኙ እንስሳት አልፎ አልፎ የሐሞት ጠጠር ይፈጠራል፤ ሆኖም ይህ ነገር በተለምዶ ወርቅ ይባል እንጂ ወርቅ አለመሆኑን ያስረዳሉ።

ፕሮፌሰሩ፥ እንደዚህ ዓይነቱ የሀሞት ጠጠር  ወደ ቻይናና ጃፓን አገር እንደሚሸጥ እንደሚያውቁ ጠቁመው ለምን አገልግሎት እንደሚውል ግን በትክክል እንደማያውቁ ነው የተናገሩት።

የወርቅ ባለሙያው አቶ አለልኝ ማተቤ ራሳቸው ከዚህ በፊት ከእንስሳት የተገኘውን ይህን የአሞት ጠጠር እስከ 80ሺህ ብር ገዝተው እስከ 100ሺህ ብር ሸጠው እንደሚያውቁ አመልክተዋል ሲል ዘገባው ያመለክታል፡፡

Exit mobile version