ETHIO12.COM

“ከአርበኝነት ውርስ ባሻገር”

የኢትዮጵያ አርበኞች 82ኛ የድል መታሠቢያ በዓል ሁሌም አዲስ ነው። የድሉ ጊዜ አንድ ዘመን ሊሞላ ቢቃረብም፣ ሁሌም አዲስ የሚሆነው በታሪኩ ግዝፈትና አሁን ድረስ አገር እያሰቃዩ ያሉ ባንዳዎች ህልማቸው እንደማይሳካ ማሳያ በመሆኑ ነው። አዲሱ ትውልድ ጀግነትን እሚማርበት፣ ኩራትን የሚቀበልበት፣ ባንዳነት ምን ያህል ነወር እንደሆነ የሚረዳበት ነው። የአርበኞች ቀን ሲከበር የዛ ዘመን ጀግኖች አጥንትና ስጋ እንደ ዜጋ በክብር ማማ ላይ ያቆመን እንደሆነ በመረዳት ነው። ከመረዳትም በላይ ከልብ የመነጨ ክብር በመስጠት ነው። ሲሻገርም ዓላማውን እንደ ዘመኑ በሟሟሸት የመረከብ ቃል በመግባትም ነው። ከአርበኛነት ውርስም ባሻገር ማየት ድግ ነው። ከስር ያለውን ያንብቡ

የኢትዮጵያ አርበኞች 82ኛ የድል መታሠቢያ በዓል ከመከላከያ ገጽ የተወሰደ

“አብሮነት ለፅናት እና ለድል” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው የድል በዓል ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አባትና እናት አርበኞች ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች ፤ የሰራዊቱ ተወካዮች ፤የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ፤ ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሀገር በማያቋርጥ የትውልድ ቅብብሎሽ እየተገነባች በአዳዲስ ታሪክ ሁነት እየጎላች የምትቀጥል መሆኗ ይታወቃል። ትላንት ለኢትዮጵያችን ነጻነት በዱር በገደሉ በጀግንነት ተዋድቀው ያስከበሩንን አባቶቻችንን መዘከር የሀገራዊ ታሪክ ውርርስ አካል ነው።

ለሀገር ብሄራዊ ፍላጎትና ጥቅም ብሎም ለኢትዮጵያችን ሰላምና ክብር በተጠንቀቅ ዘብ ቆሞ የሚገኘው ጀግናው የኢትዮጵያ ወታደርም፤ከአያት አባቶቹ አርበኝነትን በክብር የወረሰ ነው። ትውልድ እንደየዘመኑ እውነታ የራሱ ቀለም አለው። ከ82 ዓመታት በፊት የነበረው ሀገራዊ እውነታችንና አሁናዊው የሀገራችን እውነታ ይለያያሉ።

ያኔ ጣሊያን በዳግም ወረራው ቂም ቋጥሮ በማንበርከክ ተስፋ የመጣ ጊዜ፤ወቅቱ ይጠይቅ የነበረውን ጽናትና ጀግንነት አንግበው የተዋደቁልን አባቶቻችን የዘመኑን ግዴታቸውን በአኩሪ መስዋዕትነት መወጣት ችለዋልና ታሪካቸው በህያውነት እየተከበረ ነው።ሲከበርም ይኖራል።

የጀግኖች አርበኞቹን ጽናት፣አይበገሬነትና ድል አድራጊነትን የወረሰው የአሁኑ መከላከያ ሠራዊታችንም በዘመኑ ቀለምና ነባራዊ እውነታ ላይ የተመሠረተ ታሪክ በመከወን ላይ ይገኛል።

ብርቱ ፈተናዎችንን እልህ አስጨራሽ የሞት ሽረት ትንቅንቆችን በታላቅ ቆራጥነትና ተጋድሎ በድል የተወጣው መከላከያ ሰራዊታችን ስለ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ክብርና ሁለንተናዊ ዕድገት መቀጠል ሲል የከፈላቸውና እየከፈላቸው የሚገኙ መራር መስዋዕትነቶች በመጪው ትውልድ በኩራት ሲወሱ የሚኖሩ ናቸው።

ሀገርን በጫጫታ ለማፍረስ ያለ አንዳች ይሉኝታ አይናቸውን በጨው አጥበው የሚያደናቁሩ ኢትዮጵያ ጠል ሃይሎችን ህልም እያመከነ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ በክብር የምትሸጋገር ኢትዮጵያን ለማጽናት ያለ ዕረፍት ተልዕኮውን የሚወጣው ሠራዊታችን በሀገሩ መጻኢ-መልካም ተስፋ ላይ የጸና እምነት አለው።

ከትላንት አባቶች ከወረሰው አርበኝነት ባሻገር፤ ከሀገር በዘለለ ቀጠናዊ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የውትድርና ጥበብና ሳይንስን በተላበሰ ዘመናዊነት በእውቀትና ክህሎት አይደፈሬ ሀገርን እውን የማድረግ ፈጣን ጉዞው ቀጥሏል።

እናም በራሱ የዘመን ቀለም የራሱን ታሪክ በአንጸባራቂ ድሎች ታጅቦ እያነበረ የሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፤ ሀገር የማጽናት ተግባሩን ትላንት ለሀገራቸው ቀናኢ ሆነው በዱር በገደሉ ተዋድቀው ነጻነታችንን እንዳላስደፈሩት አርበኞቻችን ሁሉ በጥልቅ የሀገር ፍቅር የተሞላ ነው።

አስቻለው ሌንጫ ከአገር መከላከያ ገጽ የተወሰደ

……………………………………………………………

“አርበኝነት ሀገርን በፍቅር መውደድና ያንንም በተግባር ማሳየት ነው” ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ አበበ

ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ አበበ ትውልድና ዕድገታቸው ሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ላይ እንዳሉ የሶማሊያ ጦር ሀገርን ሲወር 1969 ዓ.ም ወደ ካራማራ ማቅናታቸውን ይናገራሉ፡፡ ከዚያ በኋላም ለ14 ዓመታት በውትድርና ሙያ ሀገሬን በፍቅር አገልግያለሁ ሲሉ ነግረውናል፡፡

በዓድዋ ፣ በካራማራና በሌሎች ሀገር ላይ በተቃጡ ወረራዎች ሀገራችን ድል ያደረገችው አባቶቻችን በፍጹም የሀገር ፍቅርና አንድነት ስሜት በመዝመታቸው ነው የሚሉት ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ ይህም ከጦር መሣሪያ በላይ ዋጋው ትልቅ እንደኾነ ያነሳሉ፡፡

ቀደምት አባቶቻችን ቤትና ቤተሰብ ሳይሉ ሀገራቸውን በፍቅር ይወዱ ስለነበር ያንንም በተግባር ማሳየታቸውን ሻለቃ ባሻ ስንታየሁ አስታውሰዋል። እኛም በነበርንበት ዘመን ያንን አድረገናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የአርበኞች ድል መታሰቢያንም ኾነ ሌሎች በዓላትን ከማክበር በዘለለ ያንን ታሪክ ማስረዳትና በወቅቱ የነበረውን ኢትየጵያዊ አንድነት የተረዳ ማኅበረሰብ መፍጠር ይገባል ነው ያሉት፡፡

እኛ ለሀገር ሉዓላዊነትና ክብር የከፈልነው መስዋዕትነት ከቀደሙት አባቶች የተማርነው በመኾኑ የአሁኑ ትውልድም ከእኛ ሊማርና የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቆ የማወቅ ኀላፊነት አለበት ሲሉ ይናገራሉ፡፡

ለኢትዮጵያ ነጻነትና ሉዓላዊነት መከበር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገር ፍቅር ስሜት ያስገኘውን ድል ሌሎች ሀገራትም ምስክርነታቸውን የሰጡት የአንድነታችን ውጤት መኾኑን ልናውቅ ይገባል ነው ያሉት፡፡

አሁን ለውስጣዊ አንድነታችን መጠናከር ከቀደሙ ታሪኮችና አባቶች ልምድ መውሰድ የሚገባን ጊዜ ላይ በመኾናችን ሀገርን ማዕከል ያደረገ ተግባቦት ሊኖረን ይገባል ሲሉ ሻለቃ ባሻ ስንታሁ አበበ አመላክተዋል፡፡

ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋዬ / አሚኮ

የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞን አስተዳዳሪዎች …
ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
ዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ ስምምነቱ መክሸፉንና …
መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ …
“ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው
የሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው ግን በሃፍረት ስሜት ነው። ያፈርኩት ደግሞ …
ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ሲኖር መሳሪያ ሸጦ …
Exit mobile version