Site icon ETHIO12.COM

ዘመድኩናዊነትን ያሸነፉ አባት !

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በቅርብ ጊዜ የወረራት ፣ የተጣባት ቫይረስ ዘመድኩናዊነት ይባላል። ዘመድኩናዊነት እንደ ቀደመው ዘመን ፈሪሳዊነት 99.9% ጊዜውን የሚያጠፋው የእግዜሩን ቃል በማካፈል ፣ ቀን የጎደለባቸውን ደገፍ ማድረግ ላይ አይደለም። ዘመድኩናዊነት አሳዳጅነት ፣ ስድነት ፣ ተሳዳቢነት ነውርን ክብር አድርጎ አደባባይ የመውጣት ህመም ነው።

ዘመድኩናዊነት ባይኖር ኖሮ ዛሬ እነ መምህር በጋሻው አጠፉ ለሚባሉት ይቅርታ ጠይቀው ቤተክርስትያኒቱን አማኙን ባገለገሉ ነበር። ዘመድኩናዊነት ባይገን ኑሮ ዛሬ መነኩሴው ፣ ዘማሪው ፣ ሰባኪው ውሎውን ቲክቶክ ፣ ፌስቡክና ዩቱይብ ላይ ባላደረገ ነበር። ዘመድኩናዊነት በጓዳ የሰማኸውን የጓደኛህን ህጸጽ በአደባባይ በሞንታርቦ ለህዝብ የማወጅ ነውረኝነት ነው።

አቡነ ጴጥሮስ ክርስትናን ሊኖሩት የሚሞክሩ ፣ የሚታትሩ ክህን ናቸው ስል አስባለሁ ። አቡነ ጴጥሮስ እና ካህናት ወዳጆቻቸው እነ አቡነ ሳዊሮስን ረግሞና አዋርዶ ከቤተስኪያን ከማራቅ ይልቅ ይቅርታን ፣ ክርስትያናዊ ወንድማማችነትን ለምዕመኑ ያስተማሩ ይመስለኛል። አቡነ ጴጥሮስ በትናንትናው ንግግራቸው የማህበራዊ ሚዲያን አጥፊነትን በገደምዳሜም ጠቆም አድርገዋል ። የዚህ ዘመን ምዕመን መንፈሱ ለዘመድኩናዊነት ቅርብ ነው ፣ ትናንት አባ ያላቸውን ካህናት ዛሬ በመንደር ቃል ለመዘርጠጥ ሰከንዶች አያመነታም። ብዙው አማኝ የእግዜሩን ቃል ከማዳመጥ ፣ በየሰፈሩ ቀን ለጎደለባቸው የሚላስ የሚቀመስ ከማካፈል የቤተስኪያን ጠላቶች የሚላቸውን ቢያሳድድ ለአምላኩ ትልቅ ውለታ የሚውል የሚመስለው ነው።

ክርስትና ሌሎችን መውደድ ፣ ደከም ያሉትን ( በመንፈስም በስጋም ) ማገዝ ነው። ክርስትና ውስጡ የአሳዳጅነትና ከሳሽነት መንፈስ ፍጹም የለበትም። አቡነ ጴጥሮስ ውስጥ ፍቅርና ትህትና የሞላበት ክርስትናን አያለሁ ።

መምሬ Samson Michailovich እንደጻፉት !

Exit mobile version