በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የስፑትኒክ አለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ÷ በሩሲያ – አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።
በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።
ማስሎቭ አክለውም በአዲሱ ልዩ መርሐ-ግብር በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ዮሩባ ቋንቋን የሚያስተምሩበትን ዕድልም እየተመቻቸ መሆኑን ነው የገለፁት።
ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ፍጹም የተለዩ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ አንድ ትልቅ አህጉር ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ህብረ ብሔራዊ ማንነቶች ያሉባት አህጉር መሆኗን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡
ሩሲያ የአፍሪካ ልሂቃን ዲግሪ ለማግኘት ከሚሄዱባቸው አገሮች አንዷ እንደነበረች ያነሱት በውይይቱ የተሳተፉት ምሁር ቱንዴ አጂሌዬ÷አሁን ላይ ሩሲያ እና አፍሪካ የትምህርት ልውውጡን መቀጠል አለባቸው ሲሉ አክለዋል።
እንደ ምሁሩ ገለጻ በግብርና፣ በኃይል እና ኢንቨስትመንት ላይ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት በመስጠት ተናግረዋል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ መከራዋን ለመካፈል አይደለም፤ በተቃራኒው እንጀራዋን በልተው ተረከዛቸውን አነሡባት” ሲሉ ጠቅላይ… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም ነው፣ ወንጀለኛ መኾን ግን ሐጥያት ነው ብለዋል፡፡ እህትና ወንድም፣ እናትና አባትን አጎሳቁሎ ገንዘብ… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ በቀላሉ ይከፋፈል ነበር። ሐኪሜ የብረት ማዕድን አዘዘልኝ። ኪኒኖቹን መውሰድ ጀመርኩ፤ አመጋገቤንም አስተካከልኩ። ብዙም ሳይቆይ… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞን አስተዳዳሪዎች የተባሉ ሁለት ዓይነት መረጃዎች እየሰጡ ነው። መንግስት ግን… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ ስምምነቱ መክሸፉንና መንግስት ውሉን እንደተወው፣ የሶማሌ ማንግስትም መንግስት በአደባባይ ስምምነቱን… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት