ETHIO12.COM

ኤርትራ ከፕሬዚዳንት ኢሳያ በሁዋላ እንዴት ትመራ የሚል የምክክር ጉባኤ ተጀመረ፤

“በኤርትራ ያሉ አፋሮች የከፋ በደል ስለሚፈጸምባቸው ወደ ኢትዮጵያና ጅቡቲ እየሸሹ ነው”

ኤርትራን ለሶስት አስርት ዓመታት የመሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በትረ ስልጣን ከያዙበት ቀን አንስቶ ምርጫ ተደርጎ አያውቅም። ስለ ምርጫ ወሬም ሆነ ተቋም ምንም አይሰማም። ኤርትራ ህገመንግስትም የሌላት አገር እንደሆነች ይተቻል። አሁን ላይ “ኤርትራ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ በሁዋላ እንዴት ትመራ” የሚለው ጉባኤ ይህን ጉዳይ ቢያነሳም ይህን ጊዜ ለምን እንደመረጠ የትብራራ ነገር የለም።

የጀርመን ድምጽ አማርኛ ክፍለጊዜ እንዳለው ከሆነ ይህ የተለያዩ ወገኖችን ያካተተ ጉባኤ ተጀምሯል። ውጤቱና ድምዳሜው ለጊዜው ባይታወቅም ተሰብሳቢዎቹ ” ከኢሳያስ በሁዋላ ኤርትራ እንዴት ትመራ” የሚለውን አጀንዳ አንስቶ አቋም ለመያዝ መሰየማቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ትህነግ ቀደም ሲል የኤርትራን መንግስት የሚረከብ የሽግግር መንግስት ማቋቋሙና ምንም ሳይፈይድ መበተኑንን የሚያነሱ “ዛሬ ምን ተገኝቶ” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። አክለውም አሜሪካ ምክር ላይ የተቀመጡት ጉባኤተኞች ማን አሰባሰባቸው? ማንስ ነው ከሁዋላቸው ያለው ይላሉ። የጀርመን ድምጽ ዘገባ እንዳለው ጉቤውን ያደራጀው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ሲሆን መሪውም አሕመድ የሱፍ መሐመድ ናቸው።

ጉቤውን አስመልክቶ ከኤርትራ መንግስት በኩል የተባለ ነገር የለም። የቀይ ባህር አፋር የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ጅቡቲ የሚኖሩ ሲሆን በተደጋጋሚ አሰብ ሃብታቸው እንደሆነና ከኤርትራ መንግስት ጋር መቀጠል እንደማይፍለጉ በተደጋጋሚ ሲያስታውቁ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የጀርመን ድምጽ ዘገባ የሚከተለው ነው።

ኤርትራ ዉስጥ ሁሉም የሐገሪቱ ዜጎች እኩል የሚሳተፉበትና የሚጠቀሙበት ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚመሰረትበትና ፍትሐዊ ሕገ መንግስት በሚረቀቅበት ስልት ላይ የሚነጋገር ጉባኤ ነገ ሐሪስበርግ- ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ተጀምሯል። የኤርትራ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የኤርትራዉያን ወዳጆች፣ የፖለቲካ ተንታኞችና ምሁራን የሚሳተፉበት ጉባኤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሚመሩት ሥርዓት በኋላ ሐገሪቱ በምትመራበት ፖለቲካዊ ስርዓት እንዴትነት ላይ ይመክራል። ጉባኤዉ ጥናታዊ ፅሑፎች፣ መረጃዎችና ምክር ሐሳቦች ይቀርቡበታል ተብሏልም።ጉባኤዉን ያዘጋጀዉ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) እንደሚለዉ በስልጣን ላይ ያለዉ የኤርትራ መንግስት በሐገሪቱ ሕዝብ ባጠቃላይ በተለይም በኤርትራ አፋሮች ላይ የሚያደርሰዉ ግፍና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነዉ። የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ፕሬዝደንት አሕመድ የሱፍ መሐመድ፤

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ፕሬዝደንት አሕመድ የሱፍ መሐመድ እንዳስታወቁት በደንከሊያ (አፋር) ሕዝብ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና በደል በመሸሸሽ የሚፈናቀለዉና የሚሰደደዉ ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ  መሆኑን ተናግረዋል። ከ200 ሺሕ የሚበልጥ የኤርትራ አፋር ሕዝብ ወደ ኢትዮጵያ፣ጀቡቲና ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰድዷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ኤርትራዉያንን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸዉ በግድ አግዟል የሚል ስለሚባለዉ ዜናን ሰምተዋል። 

የኤርትራን ጉዳይ በተለይም የኤርትራ አፋሮችን አኗኗር የሚያጠኑት ካናዳዊዉ የሕግ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ኤሊዮት ማግንት በበኩላቸዉ የኤርትራ መንግስት በኤርትራ አፋሮች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ማድረሱን ጉዳዩን በተለያየ ጊዜ ያጠኑ «የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል» ይላሉ። ማግነት አክለዉ እንዳሉት የኤርትራ መንግስት የፀጥታ ኃይላት የአፋር ተወላጆችን በጅምላና በተናጥል

ይገድላሉ፣ደብዛቸዉን ያጠፋሉ፣ሴቶቹን ይደፍራሉ።የኤርትራ መንግስት ሕዝቡን ከነባር ቀየዉ እየነቀለ አካባቢዉን እየተቆጣጠረ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አስታዉቀዋል። 

አቶ አህመድ የሱፍ በመቀጠል ዛሬ የሚካሄደዉ ጉባኤ ፤  የኤርትራ መንግስት ያደርሰዋል የሚባለዉን የሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና በዝርዝር ተነጋግሮ ለወደፊቱ ሁሉንም የሚያሳትፍ፣ ሁሉንም በሚያግባባ ሕገ-መንግስት የሚመራ ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት የሚቻልበትን ስልት ይተልማል ተብሎ ይጠበቃል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በባድሜ ድንበር አቅጣጫ መጠነኛ የተኩስ ምልልስ እንደነበር የትግራይ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን አመልክተዋል። ከሻዕቢያ ጋር በተከታታይ ቀናት የተኩስ ምልልስ መደረጉን የገለጹት ምንጮች ተኩሱ ውጊያ የሚባል ሳይሆን የትንኮሳ አይነት ነበር። አሁን ላይ ምንም ተኩስ አይሰማም።

ከዙህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ ባይታወቅም የትግራይ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው ከመከላከያ አዛዦች ጋር ስብሰባ መቀመጣቸው ተሰምቷል። የስምምነቱ አካል በሆነው ዳግም ወደ መከላከያ የሚመለሱ ቢኖሩም፣ መንግስት በይፋ ምክንያቱን አላስታወቀም። ኢትዮጵያ የባህር ሃይሏን አዘምና ለማንኛውም ግዳጅ ብቁ ማድረጓን ማስታወቁም አይዘነጋም።

Exit mobile version