Site icon ETHIO12.COM

“ጌታቸው ረዳ ዛሬም መንታ ምላሳቸው እንደተሳለ ነው”

በወረራው ወቅት ዓለም አድሞ ኢትዮጵያ ላይ ባዘመታቸው ሚዲያዎች፣ ትህነግ ራሱ ባቋቋማቸው የማህበራዊ መገናኛዎችና ለትህነግ ተከፍሏቸው በሚሰሩና አሜሪካ፣ እንግሊዝና ጀርመን በከፈቷቸው የጥቅማቸው ማስከበሪያ ጣሚያዎች ያለ ከልካይ የቃላት ሚሳይል ሲረጩ የነበሩት አቶ ጌታቸው አሁንም ባለ ምነታ ምላስ መሆናቸው በማስረጃ እየተገለጸ ነው።

የትግራይን ወጣት፣ ሙት፣ ቁስለኛ፣ አካለ ጎዶሎነት ከዳረጉት በህይወት ያሉ አመራሮች መካከል አንዱና ዋናው እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ጌታቸውን ጨምሮ ድፍን የትህነግ አመራሮች ለፍርድ መቅረብና በትግራይ ህዝብ መዳኘት ይገባቸው እንደነበር በተደጋጋሚ አሁን ድርርስ የሚገልጹ አሉ።

ትህነግ በክህደት የጀመረው ጦርነት የትግራይን እናቶች ልጅና ጠዋሪ አልባ፣ በውጭ ሆነው ጦረንቱን ሲያግሙ ለነበሩ የሃብት ምንጭ ሆኖ የተገባደደው ጦርነት መጨረሻው ወደፊት ይፋ ከሚሆነው ዘግናኝ ኪሳራ በሁዋላ “በአድኑኝ” ጩኸት መጠናቀቁ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የትግራይ መሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ምድር ላይ ያልተሰሙትን የማቆሸሺያ ቃላቶች ሳይቀር ተጠቅመው ሲዛበቱባቸው በነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ፊት ይቆማል የሚል ግምት አልነበረም።

“የካድሬን ባህሪና የሰውነት ደረጃ ማሳያ ሆነው ለቀጣዩ ትውልድ ማስተማሪያ ከሚሆኑት ወራዳዎች መካከል አቶ ጊታቸው አንዱ ናቸው። የፊልም ጠበብቶች በሰነድነት የሚቀመጥ ሙሉ ዶክመንታሪ ፊልም ሊሰሩ ይገባል” ሲሉ አቶ ደምሰው ሃይሉ የተናገሩትም ለዚሁ ይመስላል። ነውም።

በሂደት ከሃሰትና ከቅጥፈት ስብከት ጋር ተጋብተው ህሊናቸውን ያነጠፉት አቶ ጌታቸው ” ነገር በዓይን ይገባል” እንዲሉ ጸሃይ ቀርቶ በቂ ብርሃን በሌለበት አዳራሽ አይናቸውን በትልቅ የጠርሙስ መነጥር እየሸፈኑ ለህዝብ ሌላ፣ ለትግራይ ወጣቶችና አሁን ድረስ የትህነግ ፍቅር ለሚያንዘርዘራቸው የድንጋይ ዘመን አሳቢዎች ሌላ እያወሩ ነው።

አስፋው አብርሃ እስር እስራቸው እያለ በቃል በቃል ትርጉም ቪዲዮ እያመስካረና መረጃ እያደረገ ካቀርበው የአቶ ጌታቸው መንታ ምላስ አሁንም እንዳልዶለዶመ ለማሳያ ይህን ለማጋራት ወደድኩ። የትህነግ ፍቅር ለሚያንዘፈዘፋቸው አስተዋይነትን እየተመኘሁ፣ በትግራይ ህዝብ ማገዶነት ሲነገዱና ሃብት ሲያሰባስቡ ለነበሩ፣ አሁንም ፊታቸውን ቀይረው ገንዘብ ለቀማ ላይ ሙጭጭ ላሉ ቢያንስ አካለ ጎዶሎ ለሆኑት ምስኪኖች ሲሉ ወደ ቀላባቸው እንዲመለሱ ከሰሙ ምክሬን እለግሳለሁ። አስፋው ካዘጋጃቸው ውስጥ የሚከተለውን እዩልኝ። እውን አቶ ጌታቸው መሪ ናቸው? ሚሊዮኖች ደምና አስከሬን ላይ ቆመው ስለ እርቅና ምህረት የሚያወሩት በዚህ ልቡናቸው ነው? እንዲህ ባሉ ሰዎች የትግራይ ህዝብ ስንት ዓመት፣ ስንት ጊዜ ይታለላል? ለምን ያህል ዘመን ነው መቃብር የሚያየው? ከወዳጆቹና ጎረቤቶቹ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ እንዲኖር የሚፈረድበት? እስከመቼስ ነው “እምቢ” የማይለው? እስከመቼ ነው ልጆቹን በትህነግ ጨርቅና ፕሮፓጋንዳ እየጠቀለለ የሚቀብረው? መቼ ነው የትግራይ ምሁራን ” በቃ” ብለው የማይነሱት? በትግራይ ህዝቡን ያደነዘዘውና ያሳወረው ምን ይሆን?

ትርጉም፤ በአስፋው አብርሃ

አቶ ሰላሙ ሃይሌ አስፋው አብረሃ የተረጎመውን በማያያዝ ከላኩት መጠነኛ እርማት ተደርጎ በነጻ አስተያየት የተለጠፈ፤

Exit mobile version