Site icon ETHIO12.COM

ቴድሮስ አድሃኖም “የአማራ ክልል አሳሰበኝ” አሉ

አማራና አፋር ክልል በወረራ አመድ ሲሆን ትንፍሽ ያላሉት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ በአማራ ክልል በተከሰተው ግጭት መንገዶች መዘጋታቸው እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ የሰብዓዊ እርዳታን ማድረስ እና ግንኙነትን ለማስቀጠል ከባድ እንደሚያደርገው አመለከቱ። ሃዘናቸውን መግለጻቸው ደግ ቢሆንም በርካቶች ” የካድሬ ስብዕና ያስደንቃል” ሲሉ፣ ቀደም ሲሉ በነበራቸው የታጋይነት አቋም ሲዘልፏቸው የነበሩ ዜናቸውን እየተቀባበሉት ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ገጻቸው ይህን ያሉት በአማራ ክልል በታጣቂዎች እና በመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች መካከል የተከሰተው ግጭት ተከትሎ ነው።

 የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ግጭቶች በሰዎች ጤና ላይ በፍጥነት አሉታዊ ተጽእኖ ከማሳደራቸው በተጨማሪ በጤና ስርዓቱ ላይ ረዥም ጊዜ የሚዘልቅ ጉዳት ያስከትላሉ ብለዋል። ስጋታቸው ትክክል ቢሆንም ቴዎድሮስ ትህነግ አማራና አፋርን ወሮ ሲያወድም፣ ክሊኒክና ሆስፒታል ሲዘርፍና ሲያቃጥል ይህን አላሉም።

ዶ/ር ቴድሮስ ሰዎች የጤና ድጋፍ እንዳይቋረጥባቸው እና የዓለም ጤና ድርጅት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ሥራቸውን ማከናወን እንዲችሉ በክልሉ የጤና ስርዓቱ ጥበቃ እንዲደረግለት ጠይቀዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም “ከምንም በላይ ለሰላም ጥሪ እናቀርባለን” ማለታቸውን ቢቢሲ ነው የዘገበው። ትህነግ ተሸንፎ የሰላም ስምምነት ካደረግ በሁዋላ አደብ ገዝተው የተቀመጡት ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁን ላይ የሰጡት መግለጫ ሳይሆን ቀደም ሲል ” እኔ ወያኔ ነ” እስከማለት ደርሰው ሲያስተላለፉ የነበሩት መረጃና አቋም ምን ግዜም ቢሆን ተዓማኝ እንደማያደርጋቸው ብዙዎች መግለጫውን ተከትሎ ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት በአማራ ክልል ጨምሮ በጤና ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሎ እንደነበር የገለጸው ቢቢሲ ሃላፊ በወቅቱ በትህነግ አባልነታቸው ታውረው የአማራና አፋር ህዝብን ስቃይ በዝምታ ያልፉት እንደነበር አልተቆመም።

በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን በሚያስተናግደው ክልል የመድሃኒት እና የህክምና ቁሳ ቁስ ግብዓት እጥረት ከሰላም እጦት ጋር ተደማምሮ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንቅስቃሴን ገድበው ቆይተዋል።


Exit mobile version