Site icon ETHIO12.COM

ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው ትላንት መግለጫ ሰጥተዋል።

ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦
1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት (ደብረ ማርቆስ)
2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ስቴም (STEM) ትምህርት ቤት
4. ሀይራንዚ አዳሪ ትምህርት ቤት (ስልጤ ዞን)
5. ሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (ሀድያ)
6. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት (ናዝሬት)
7. ኮተቤ ሼርድ ካምፓስ
8. የኔታ አካዳሚ
9. ወላይታ ሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት
10. ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት

ሀናን ናጂ አህመድ

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።

ተማሪ ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች።

ባስመዘገበችው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኗን የገለጸችው ተማሪ ሀናን፤ በቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደመትተጋ ተናግራለች።

ክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ነው።

ወላይታ ሊቃ

ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካስመዘገቡ አስር ትምህርት ቤቶች መካከል 9ኛ ደረጃ አጊኝቷል።

ትምህርት ቤቱ በ2015 ዓ.ም ካስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ውጤት ያመጡት፦
• ከ600-623 ➧3 ተማሪዎች
• ከ500-599 ➧ 26 ተማሪዎች
• ከ400-499 ➧ 31 ተማሪዎች
• ከ350-399 ➧ 12 ተማሪዎች
• ከ324-345 ➧ 4 ተማሪዎች

“በሚቀጥለው ዓመት የሚሰጠው ፈተና ድብልቅ ፈተና ይሆናል። ግማሹን በኦንላይን፣ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ በአካል ይሰጣል።” @tikvahuniversity

ይህ ያለንበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ፤ ለምን በማሰብ እና በዕውቀት እንደማንመራ የሚያሳይ፤ ለምን ሌብነት የተንሰራፋባት አገር እንደሆንን፤ ዘረኝነት ለምን የሙጢኝ ብለን እንደያዝን፤ በማኅበራዊ ሚዲያ በየዕለቱ የሚዋሹንን ሳናገናዝብ እንደምንሰማ፤ የወሬ ሰለባ ለምን እንደሆንን፤ ወዘተ ባጠቃላይ የማንነታችን መገለጫ ይህ በያመቱ የሚወጣ ፈተና ውጤት ነው። ጥያቄው ያ ሁሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠናቀቀ ተብሎ በየዩኒቨርሲቲው ተመርቆ ሲወጣ የነበረባት አገር ምነው አሁን ከምታስፈትነው ውስጥ ከ3በመቶ ያላለፈ ተማሪ ለዪኒቨርሲቲ ማብቃት አቃታት?

መዘንጋት የሌለበት ሐቅ ይህ ሁኔታ ጀመረ እንጂ አያቆምም፤ ላለፉት 30 ዓመታት ሲፈርስ የነበረ ተቋም ባንድ ጀምበር ተዓምር አይሠራም፤ የሚቀጥለው ዓመትም ውጤት ከዚህ የሚለይ አይደለም። አሁን ዘጠነኛ ክፍል ያሉት ተማሪዎች ወደ 10ኛ ክፍል ሲደርሱ ነው ለውጥ ማየት የምንጀምረው። የትሕነግ ወንበዴዎችን መርቶ ለሥልጣን ያበቃው የምዕራባውያን ድጋፍና የ30 ዓመታት የትሕነግ የክፋት መርዝ በቶሎ የሚለቅ አይደለም። በትንሹ አንድ ትውልድ አክሽፎ እና ቀጣይ ትውልዶችን መርዞ ነው ያለፈው። ይህ እስከሚጸዳ ዓመታት የግድ መውሰዱ አይቀርም። የተጀመረው ተሃድሶ ሳይደናቀፍ ማስቀጠል መቻል በራሱ ታላቅ ዕድል ነው።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ


Exit mobile version