ለተማሪዎች መውደቅ ማነው ተጠያቂው ?

በህ/ተ/ም/ ቤት የሰዉ ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፦

” … ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወደራሱ መውሰድ አለበት በምንልበት ጊዜ ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮዎችን የሚመሩና እስከ ወረዳ እስከታች ድረስ እንዲሁም የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት ደረጃ ምን ያህል Shock ሆነዋል ?

ተማሪው እና ወላጁ ብቻ ነው እንጂ ይሄንን እዳ የተሸከመው ሁሉም ባለበት እየሄደ ነው ማንም ኃላፊነት እየወሰደ አይደለም።

ምንድነው እየተወሰደ ያለው እርምጃ ? የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከዛም እስከ ታች ያሉ ዳይሬክተሮች ሁሉም በነበረበት ቀጥሏል። በቃ ተማሪ አለፈ አላለፈ ጉዳያቸው አይደለም፤ ምንም አይቀነስባቸውም ምንም ማስጠንቀቂያ የለም ተማሪ አላሳለፈ አሳለፈ ጉዳዩ አይደለም።

እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ መቀጠል አለብን ወይ ? አይደለም ይሄንን ቢያንስ ተጠያቂነት መኖር አለበት ብሎ የሆነ ነገር ማድረግ ያለበት ትምህርት ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የሚሰሩ የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የቢሮ ኃላፊዎች ናቸው። “

ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ተጨማሪ ምን አሉ?

  • በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ96 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና በላይ ይማምጣት አለማቻላቸው እንዲሁ እንደኖርማል የሚወሰድ አይደለም። ይሄን ያህል ተማሪ አለማለፉ እንድምታው ቀላል አይደለም።
  • በዚህ ነገር ተጠያቂ የሚሆነው ” ሁሉም ነው ” የሚለው ነገር አይቸጋሪ ነው። ተጠያቂው everybody ሁሉም ነው ነው ከተባለ nobody ማንም ነው ማለት ነው።
  • ” ሁሉም ተጠያቂ ነው ” ማለት እነማናቸው ሁሉም ? ሁሉም የሚለው መፍትሄ አያመጣም። ወላጅ የራሱ ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቢሮ በየደረጃ ከሆነ ያግባባናል።
  • በሀገር ደረጃ አስፈፃሚዎች (እንደ ገንዘብ፣ ጤና…ሚኒስቴሮች) የተደራጁት በራሳቸው ተልዕኮ አኳያ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው ተልዕኮ ይሄ የኔ ውድቀት ነው ብሎ መውሰድ አለበት።
  • ትምህርት ሚኒስቴር ውድቀቱ የኔነው ብሎ ሲወስድ በስሩ ያሉ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ቢሮዎችን ጨምሮ ነው።
  • እነዚህ ተማሪዎች ከታች ጀምሮ 50 በመቶና በላይ እያመጡ ነው እዚህ የደረሱት ይህ የሚያሳየው ከታች ጀምሮ የምዘና ስርዓቱ ችግር እንዳለበት ነው። የትምህርት አሰጣጡም ችግር አለበት። አንዳንዶቹ እራሳቸው የማያውቁት እንዲያስተምሩ ይደረጋል፤ አንዳንዶች ደግሞ ኮሌጅ ሳይገቡ፣ ዲፕሎማ ዲግሪ ሳይኖራቸው የሀሰት ማስረጃ አሰርተው ዓመታት ሲያስተምሩ የቆዩ መኖራቸንም በሚዲያ ሰምተናል። ስለዚህ አጠቃላይ ስርዓቱ መፈተሽ አለበት።
  • ከታች ጀምሮ ብቁዎች ብቻ ለ12ኛ ክፍል እንዲቀመጡ እያደረግን ነው ?
  • ኩረጃ ስላስቀረን ነው ተማሪው የወደቀው የሚለው ሁሉንም ላያስምን ይችላል። በተወሰነ ደረጃ እውነት ነው።
  • ተማሪዎች ለምን እንደወደቁ ይጠና። #ገለልተኛ ምሁራን የተካተቱበት ጥናት ይደረግና በዋናነት ተማሪዎች ለምን እንደወደቁ ይታወቅ፤ ሌሎችም ምክንያቶች ካሉ ይጠና።  እንዴት ይሄን ማስተካከል እንደሚቻል መፍትሄ ይመላከት። ያለዛ መፍትሄ አይገኝም።
See also  ጥሪ ለአለም«በትግራይ ግድያና ስቃይ በመበራከቱ ነዋሪዎች ወደ ኤርትራና ሌሎች ክልሎች አየተሰደዱ ነው»

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለ ገለልተኛ ጥናት ምን አሉ ?

” ገለልተኛ ጥናት ቢደረግ ለተባለው፤ ይሄ ተቋም (ፓርላማው) ገለልተኛ ስለሆነ ከተቻለ ነፃ የምሁራን ኮሚቴ አቋቁሞ ጥናቱን ለምን አያደርግም ? “

ዶ/ር ነገሪ ፤ ፓርላማው በጥናቱ ሰው ማሳተፍ እንደሚቻል ነገር ግን በባላይነት ኮሚቴ አቋቁሞ ለመስራት ከአሰራር አኳያ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ጥናቱ ለሚኒስቴሩም ግብዓት ይሆናል ማለታቸውን የትክቫህ መረጃ ያስረዳል።


Leave a Reply