Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ብሔራዊ የክብር ሽልማት ተቀበሉ፤ በታሪካ 21ኛው የክብሩ ባለቤት ሆነዋል

– መንግስት ፕሮፌሰር ገቢሳን “እንኳን ደስ አለዎት” ሲል ክብር እንደተሰማው አስታውቋል፤

ድንቁ ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኢጄታ የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን መቀበላቸው ለአገር ኩራት፣ ለወገን ኩራት በመሆኑ የደስታ መልዕክት በርካታ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ አጉርፈዋላቸዋል።

ሸዋ ኦሎንኮሚ የተወዱት ፕሮፌሰር ገቢሳ በዕጽዋት ዘረመል ማዳቀል እና ዓለም አቀፍ ግብርና ተመራማሪ፣ የፑርዱ ግሎባል የምግብ ዋስትና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፣ ሲሆኑ ሽልማቱንም ከአሜሪካ ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳሊያን ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እጅ ተረክበዋል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ብሔራዊ የክብር ሽልማት ከተሸለሙ 21 አሜሪካውያን ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ለመሆን የበቁ መሆናቸው በታሪካ ተመዝግቧል። የኢትዮጵያ መንግስትም በእኚሁ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ታሪክና ተግባር አገር መክራቷን ጠቅሶ “እንኳን ደስ አለዎት” ሲል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት መግለጫ አውጥቷል።

መምህርና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ ለሽልማቱ ያበቃቸው በከፍተኛ የምርምር ስራቸው የእፅዋት ዘረመል ምህንድስና በመጠቀም በረሃማ የአየር ንብረት እና ነፍሳትን የሚቋቋሙ የአዝርዕት ዘሮችን በማግኘታቸው ባገኙት የልህቂነት ክብር ሳቢያ ነው። ይህ ድንቅ ተብሎ ለታላቅ ሽላማት ያበቃቸው ግኝታቸው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የዓለም ፍጡራን የምግብ ዋስትናን እንደሚያረጋግጥ ያታመነበት ሆኗል።

ፕሮፌሰር ጋቢሳ ኤጄታ በምግብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከዚህ በፊት ከዓለም የምግብ ፕሮግራሙ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በተለያዩ መድረኮችም ከፍተኛ ክብር አጎናጽፏቸዋል።

ፕሬዚደንት ባይደን በይፋዊ የማህበራዊ ገጽ አውዳቸው እንዳሉት የተሸላሚዎች ዝርዝር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ ለሽልማት የበቁትን ተመራማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ በሚል አውድሰዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ሽልማቱ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ የሚከተለውን ‘ የንኳን አደረሰዎ” መግለጫ አሰራጭቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ላገኙት ለፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፏል።

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ የአሜሪካን ብሄራዊ የሳይንስ ሜዳሊያ ሽልማትን ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክቱ ሽልማቱ ፕሮፌሰሩ በዕጽዋት ዘረመል ማዳቀል ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑን ገልጿል።

ፕሮፌሰር ገቢሳ በዕጽዋት ዘረመል ማዳቀል እና ዓለም አቀፍ ግብርና ተመራማሪ፣ የፑርዱ ግሎባል የምግብ ዋስትና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፣ ሲሆኑ ሽልማቱንም ከአሜሪካ ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳሊያን ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እጅ ተረክበዋል። ሽልማቱ አሜሪካ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ ተመራማሪዎች የምትሰጠው ከፍተኛ እውቅና ነው።

ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ በማሽላ እህል ላይ ሰፊ ጥናት ያደረጉ ሲሆን እ.አ.አ በ2009 የከፋ ድርቅ እና አጥፊ አረምን የሚቋቋሙ የማሽላ ዝርያ ላይ ባደረጉት ምርምር የዓለም ምግብ ሽልማትን አግኝተዋል ።

ይህ ምርምራቸው ከፍተኛ የማሽላ ምርትን በመጨመር ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ ረድቷል።

ፕሮፌሰር ገቢሳ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ብሔራዊ የክብር ሽልማት ከተሸለሙ 21 አሜሪካውያን ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሆነዋል። በዚህም መንግስት ክብር እንደተሰማው ገልጾ ደስታውን ገልጾላቸዋል።


Exit mobile version