Site icon ETHIO12.COM

ጃዋር መሐመድ ወደ ብልጽግና ኦፌኮን ይዞ? የዳሬ ሰላሙ ንግግር መግባባት እየታየበት ነው

የኦሮሞ ፌድደራላዊ ኮንግረንስ ስራ አስፈጻሚ ጃዋር መሐመድ ኦሮሞ ብልጽግናን ለመቀላቀል እንቅስቃሴ ላይ እንዳለ የድርጅቱ አንድ ከፍተኛ አመራር ለኢትዮ12 ገልጹ። በጉዳዩ ዙሪያም በግልጽ ከጃዋር ጋር ንግግር መደረጉንም አመልክተዋል። የዳሬ ሰላሙ የሰላም አማራጭ ንግግር መግባባት እየታየበት መሆኑ ተሰማ።

በጃዋር ጥያቄ ይሁን በሶስተኛ ወገን መልዕክተኞች አማካይነት ጉዳዩ ሲቀነቀን እንደነበር ቁርጥ ያለ መረጃ ለመስጠት እንደሚችገሩ ያስታወቁት እኚሁ ሰው ” ጃዋር በኦፌኮ እንደቀድሞው ንቁ ተሳትፎ አያደርግም” ብለዋል።

“ሽማግሌው ባሉበት” አሉ የዜናው ባለቤት የኦፌኮ አመራር ” ሽማግሌው ባሉበት / መረራ ጉዲናን ነው/ ብልጽግናን ለመቀላቀል እንቅስቃሴ ላይ ነህ አይጠቅምህም። ከጠቀመህ ቀጥልበት” እንድተባለ አመልክተዋል።

ጃዋር ራሱን ብቻ ሳይሆን ኦፌኮን ይዞ ከብልጽግና ጋር አብሮ መስራት እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ መረጃ ለድርጅቱ ይደርስ እንደነበር በማመልከት በዚህ ዙሪያ ግልጽ ውይይት መደረጉን አመልክተዋል።

ጃዋር አዲስ አበባ እያለ እንኳን እንደቀድም ቢሮ እንደማይመጣ ያመለከቱት የኦፌኮ አመራር፣ በቀጥታ ባይገልጹትም በኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ህብረት የሚያመሩበት አጋጣሚ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰፋ እንደሄድ አመልክተዋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የብልጽግና ኦሮሚያ ባለስልጣኖችን ለማነጋገር ቢሞከርም ምንም ፍንጭ ማግኘት አልተቻለም። ይሁን እንጂ ፓርቲው በክልሉ ካሉ ተቀናቃኞች ጋር ስምምነት ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

ጃዋር መሐመድ ከእስር ከወጣ በሁዋላ ” የአንድነት ሃይሎች ከዱኝ” በሚል ቅሬታ ካሰማ በሁዋላ የቀድሞ አቋሙን በመቀየር ” ሰላም” በማለት ሁሉም ወገኖች ለሰላም መገዛትና መስማማት እንዳለባቸው በገሃድ አቋም ይዞ መቅረቡ በርካቶችን አነጋግሮ ነበር። ከዚህም በላይ ዝምታን የመረጠው ጃዋር ” ምን እያደረገ ነው” የሚል ጥያቄም ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው።

የኦፌኮ አመራር ” ለዝምታው ቀጥታ ምላሽ የለኝም። ይሁን እንጂ የአቋም ለውጥ ማሳየቱን ማንም አይክድም። የሚጠይቀው ቢገኝ እሱም ያምናል” ብለዋል። አያይዘውም ” በፓርቲያችን የቀድሞ እይነት እንቅስቃሴ አያደርግም። በስልክ አንዳንዴ ከቢሮና ከፕሮፌሰር መረራ ጋር ሚያደርገው ግንኙነት ውጭ እንደ ፓርቲ አመራር የጎላ ሚና አያሳይም። ይህ ግርታን ፈጥሯል። በቅርቡ መጥራቱ አይቀርም” ብለዋል።

አንዳንዶች ጃዋር የሰላም ውይይት እንዲደረግ እያመቻቸ እንደሆነም አስተያየት ሲሰጡ ነበር። ከኦነግ ጋር ብዙም ፍቅር የሌለውና በከፍተኛ ደረጃ ሲተቻቸው እንደነበር የሚያስታውሱ ” እንዴት ጃዋር ሊሰሙት ይቻላሉ። የኦነግ ሰዎች ጃዋርን አይወዱትም። ክፉኛ አውግዟቸዋል” ይላሉ። አያይዘውም ኦነግ እያለ ኦፌኮን መምረጡ የዚሁ ውጤት በመሆኑ የሰላም አመቻች ነው መባሉን ብዙም አይቀበሉም። ይሁን እንጂ ፍላጎት እንዳለው ከእስር ከወጣ በሁዋላ ሲሰጣቸው ከነበራቸው የአደባባይ ንግግሮች ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል።

ጃዋር ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንደቀድሞ እንዳልነበር የሚጠቁሙ፣ በሁለቱ መካከል የነበረው ፍቅር ምን እንደገባው አሁን ድረስ መረጃ አላገኙም። ይሁንና አቶ በቀለና ጃዋር አቶ ለማን መገርሳን ይዘው ብልጽግናን ለመጠቅለል ያደረጉት ሙከራ በዶክተር አብይ ድንገተኛ ውሳኔ ከከሸፈ በሁዋላ በሁለቱ መካከል መተማመን እንዳልነበረ ያወሳሉ።

ጃልመሮን ያካተተ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትና የመንግስት የሰላም አማራጭ ንግግር በዳሬሰላም እየተካሄደ መሆኑንን ገልጸን መዘገባችን አይዘነጋም። ጃልመሮ ካሉበት ጭካ በአደራዳሪዎች አማካይነት ሄሊኮፕተር ቀርቦላቸው ከደንቢ ዶሎ ወደ ዳሬ ሰላም መግባታቸውን ኢትዮ ስታንዳርድ ነው ቀድሞ የዘገበው። እንደ አንዳንድ ምንጮች ውይይቱ ግልጽ ባይወጣም ቀድመው የተሰሩ ስራዎች ስላሉና በህገመንግስቱ ማክበር ጉዳይ አማጺዎቹ በማስማማታቸው መልካም ውጤት ይጠበቃል።

በመጀመሪያው ንግግር ላይ ከማጺው ሃይል በኩል የተነሱት የህገመንግስት ጥሰት የታየባቸው ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ማስተካከያ ተወስዶባቸዋል። በዚህም መነሻ ንግግሩ በርካታ መሻሻል የታየበትና ለመግባባት የሚያስችል ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ንግግር መጀመሩም ተሰምቷል።


Exit mobile version