Site icon ETHIO12.COM

ታዳኙ የአልሸባብ አዝማች ማኣሊም አይማን መገደሉ ተሰማ

በሶማሌ የሚንቀሳቀሰው የአሸባሪው ዓልሸባብ ከፍተኛ አመራር ማኣሊም አይማን መገደሉን የመገናኛ ብዙሃን የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስትርን ጠቅሰው ገልጸዋል። የተገደለውም በአሜሪካ ኃይሎች ድጋፍ የሶማሊያ ጦር ባካሄደው ዘመቻ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ማኣሊም አይማን በሶማሊያና በአካባቢው ሀገራት የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን በመምራትና በማስፈጸም የሚውነጀል ነበር። በዚህም ምክንያት በጥብቅ ሲታደን ቆይቷል።

ታዳኙ ማአሊም ከሦስት ዓመታት በፊት እሱ እንደመራው በሚነገርለት ጥቃት በኬንያ ሰሜናዊ ድንበር ማንዳቤይ ወታደራዊ የዓየር ምድብ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተመልክቷል። በዚሁ እሱ በመራው የሽብር ጥቃት የኬንያውያና አሜሪካ ዜጎች መገደላቸው በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል። ጥቃቱን ተከትሎ ይህንኑ ታዳኝ ለጠቆመና ” አይሁ” ላለ አሜሪካ አስር ሚሊዮን ሚሊየን ዶላር ወሮታ እንደምትከፍል አስታውቃ ነበር።

የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸውእንዳሉት ማኣሊም አይማን በጥምር በተካሄደ ዘመቻ ተገድሏል። ይህንኑ የሚኒስትሩን መረጃ ዋቢ በማድረግ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዜናውን አሰራጭተዋል። ዓልሸባብ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

Exit mobile version