Site icon ETHIO12.COM

እስራኤል የሂዝቦላህን ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ በድሮን ጥቃት ገደለች

ከአንድ ኢራናዊ ጀነራል ጋር በሊባኖስ በምስል ታይቶ የነበረው የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥ በድኦን ጥቃት መገደሉ ተሰማ። ጥቃቱ የደረሰው ኮማንደሩ ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በተሽከርካሪ ሲንቀሳቀስ እንደሆነ እማኞችን የጠቀሰው ሬውተርስ ዘግቧል።

የሂዝቦላህ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዠ ዊሳም ታዊል በእስራዔል ጥቃት መገደሉን የሊባኖን ባለስልጣናትም አረጋግጠዋል። እስራኤል የኢራን አብዮታዊ ዘብ የጦር አማካሪ ዚያድ ራሲ ሙሴቪ በተመሳሳይ የአየር ጥቃት በሶሪያ እንድተገደሉ የሀገሪቱ ቴሌቪዝን ማስታወቁ አይዘነጋም። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እስራኤል በይፋ መግለጫ አልሰጠችም።

የሂስቦላህ ወታደራዊ አዛዡ በደቡባዊ ሊባኖስ እስራኤል በፈጸመችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መገደሉን የሊባኖስ ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆኑ ራሱ ሂዝቦላም አምኗል። ይሁንና ስለ አገዳደላቸው ዝርዝር አላብራራም።

የድሮን ጥቃቱ ዊሳም ታዊል እና ሌሎች የሂዝቦላህ አባላትን በያዘች መኪና ላይ መፈጸሙን ሬውተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ሲዘግብ እንዳለው ግድያው አሰቃቂ ነበር። ጥቃቱ የተፈጸመበትን ስፍራና ተሽከርካሪ የሚያሳዩ ምስሎች እንደሚመሰክሩት ዒላማውን በመታው የድሮን ጥቃት የተረፈ ነገር የለም።

Exit mobile version