Site icon ETHIO12.COM

በቀንዎ የሎሚ ውሃ በመጠጣት የሚጀምሩባቸው ሰባት ምክንያቶች

በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን ውስጥ የምናደርጋቸው ትናንሽ ለውጦች በጤናችን ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ለምሳሌ ቀንዎን የሎሚ ውሃ በመጠጣት ይጀምሩ።

የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶ/ር ሮክሳን ቢ ሱኮል: ይህን እጅግ በጣም ቀላል ልማድ ለመከተል የሚያስገድዱ ሰባት ምክንያቶችን ያብራራል።

1 ምግብን ለመፍጨት ያግዛል | Aids Digestion

አሲድ ምግብን ለመፍጨት ይረዳል። ለዚያም ነው በጨጓራችን ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኘው።

በሎሚ ውስጥ ያለው አሲድ በተለይ የጨጓራችንን የአሲድ መጠን ለመጨመር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።

እድሜያችን በገፋ ቁጥር የጨጓራ አሲድ የመፍጨት አቅሙን እያጣ ወይም እየቀነሰ ይመጣል።

በተለይ በዚህ ጊዜ የሎሚ ውሃ ወይም የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ለጤና ጠቃሚ ነው።

2 ድርቀትን ለመከላከል | Help You Stay Hydrated

ብዙዎቻችን ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆነ በቂ ውሃ አንጠጣም።

ጧት ላይ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምሮ መጠጣት ልማድ ማድረግ የሚያስፈልገንን የመጠጥ ውሃ ለማግኘት ይረዳል።

በቂ ውሃ መጠጣታችንን እንዴት ማወቅ እንችላለን? በሽንት ቀለማችን ጥራት ማወቅ እንችላለን (Clear Urine)።

3 ክብደትን ለመቀነስ | Weight Loss

ሰዎች ለማዳ ፍጡሮች ስለሆንን ነገሮችን በቀላሉ እንለምዳለን።

የጧት ቡና ወይም ሻይ ልምዳችንን በሎሚ ውሃ ወይም በሎሚ ጭማቂ መተካት በጊዜ ሂደት ውስጥ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል።

4 ኦክስዴሽንን ለመከላከል | Prevent Oxidation

በሎሚ ውስጡ በሽታ ተከላካይ የሆኑ ፋይቶ-ኒውትረንቶች ንጥረ-ነገሮች በብዛት ይገኛሉ።

እነዚህ ፋይቶ-ኒውትረንቶች (Phyto-nutrients) ተብለው የሚጠሩት ንጥረ-ነገሮች ከፍተኛ የሆነ የአንቲ-ኦክሲደንት ባህሪ አላቸው።

ፋይቶ-ኒውትረንቶች በኦክሲዴሽን ምክንያት የሚከሰትን የሴሎች ጉዳት ይከላከላል።

5 ጤናማ ቫይታሚን-ሲ ይለግሳል | Supplies a Healthy Dose Of Vitamin-C

የሎሚ ግማሽ ውሃ ውስጥ ጨምቆ መጠጣት ለሰውነታችን የሚያስፈልገውን ቫይታሚን-ሲ እንድናገኝ ይረዳል።

ቫይታሚን-ሲ የሴሎችን ጉዳትን ለመከላከልና ቁስልን ለመጠገን ይረዳል።

6 የፖታሲየም መጠንን ይጨምራል | Provides a Potassium Boost

ያለ ፖታሲየም ሰውነታችን በአግባቡ መስራት አይችልም። ነርቮች ከጡንቻ ጋር እንዲነጋገሩ ወይም እንዲግባቡ ፖታሲየም ያስፈልጋቸዋል።

ፖታሲየም በሰውነታችን ውስጥ ንጥረ-ነገሮችን ለማዘዋወርና ቆሻሻን ለማስወገድ ያስፈልጋል።

ፖታሲየም ጨው በደም ግፊት ላይ ያለውን ተጽእኖ በመጠኑም ቢሆን ይቀንሳል።

7 የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል | Prevent Kidney Stones

የሎሚ ውሃ በዩሪናሪ ሲትሬት (Urinary Citrate) እጥረት ምክንያት የሚከተለውን የኩላሊት ጠጠር መፈጠር ይከላከላል።

ሌላኛው የኩላሊት ጠጠር መንስኤ በቂ ውሃ አለመጠጣት እንደመሆኑ የምንጠጣው ውሃ የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል።

የሎሚ ውሃን እንዴት እንጠቀመው?

በቀላሉ ግማሽ ሎሚ በአንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ ጨምቆ መጠጣት ከላይ የተዘረዘሩትን የጤና በረከቶች ይሰጣል።

ምን ያህል? እና መቼ? የሚሉት ጥያቄዎች በእርግጥ ያን ያህል ለውጥ አያመጡም። በማንኛውም መንገድ ቢወስዱት ለጤንነትዎ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።

ምንጭ:- ክሌቨርላንድ ክሊኒክ ዶት ኦርግ

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ

Exit mobile version