Site icon ETHIO12.COM

መቅደስ ዳባ – ከከፍተኛ ጥቅም ይልቅ አገራዊ ጥሪን “እሺ” ያሉ ሚኒስትር

“ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የጤና ሚኒስትር ሆነሽ በመሾምሽ የተሰማኝን ደስታ እየገለጽኩ ይህንን ከፍተኛ ሃላፊነት በትጋት፣ በብቃት እና በርኅራኄ እንደምትወጪው ባለሙሉ እምነት ነኝ። በቀጣይ የጤና ስርዓቱን ለማጠናከርና የማህበረሰባችንን ጤና ለማሻሻል ከባልደረቦችሽ ጋር ከፍተኛ ለውጥ የምታስመዘግቢበት ውጤታማ የአመራር ዘመን እንዲሆንልሽ እመኛለሁ፡፡ በዚህም ወቅት ማንኛውንም ድጋፍ ለመስጠት ከጐንሽ መሆኔን ስገልጽልሽ በደስታ ነው” ዶር ሊያ ታደሰ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሲሾሙ ካስተዋወቋቸው መካከል ዶክተር መቅደስ ዳባ አንዷ ናቸው። አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት መቅደስ ለጤና ሚኒስትርነት ሲታጩ ከፍተኛ ጥቅም ከሚያገኙበት የዓለም ጤና ድረጅት ሃላፊነታቸው ይልቅ አገራቸውን ለማገልገል ፈቃደኛ መሆናቸው ተመል፤ክቷል።

አብይ አህመድ የዶክተር መቅደስ ዳባ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ሹመታቸውን አጽንቷል።

ዶክተር መቅደስ ዳባ በማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ባደረጉት ምርምርና አስተዋጽዖ በፈረንጆቹ 2021 በሴቶች ዘርፍ የዓለም የጽንስና ማኅፀን ሕክምና ሽልማትን ማሸነፋቸው ለሹመት ሲቀርቡ የተገለጸው ግለ ታሪካቸው ውስጥ ተካቷል። ዶክተር መቅደስ ዳባ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የተጣለባቸው ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃለ-መሃላ በመፈጸም የካቢኔ አባል ሆነዋል። ዶክተር መቅደስ ከመጋቢት 03 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ዓመታት ገደማ በስልጣን ላይ የነበሩትን ዶክተር ሊያ ተሾመን ተክተዋል። መቅደስ የብልጽግና ፓርቲ አባል አይደሉም። በጠቅላይ ሚኒስትር ካቢኔ ውስጥ የብልጽግና አባል ያልሆኑ ሚኒስትሮች አምስት ደርሰዋል።

በሌሎች ላይ ሲሆን እንደሚታየውና እንደተለመደው ዶር መቅደስም በዘራቸው፣ በማንነታቸው፣ በውሳኔያቸውና በስራቸው በጭፍን ስድብና ነቀፌታ እንደሚጠብቃቸው፣ ከሳቸው በማይሻሉ ” አላዋቂ” በሚል ትንተና እንደሚሰጥባቸው የገለጹ ሚኒስትሯ በእናታቸው የአማራ ብሄር አባል እንደሆኑ “ለመረጃ” ሲሉ አስቀድመው አሳውቀዋል።

ለመሆኑ ዶክተር መቅደስ ዳባ ማን ናቸው?

አዲስ አበባ የተወለዱት የጽንስ እና ማህጸን ሐኪሟ ዶክተር መቅደስ ዳባ ፈይሳ ባለፈው ዓመት መግቢያ ላይ በህክምና ዘርፍ ላይ ባደረጉት ምርም እና አስተዋጽኦ በሴቶች ዘርፍ የዓለም የፅንስና ማህፀን ህክምና ሽልማትን አሸናፊ ሆነዋል።

ተባባሪ ፕሮፌሰሯ ዶክተር መቅደስ ከመስከረም 2015 ጀምሮ ይህ ስልጣን እስኪሰጣቸው ድረስ የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ ሆነው እንደሰሩ የሊንክድኢን ገጻቸው ያመለክተዋል።

ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ በጳውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጅ ከ2010 ጀምሮ የማህጸን እና ጽንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ሆነው እየሰሩ ነበር።

በሌላ በኩል ከየካቲት 2012 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ጽንስ እና ማህጸን ሃኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከዚያ በኋላ ደግሞ ከመስከረም 2014 እስከ 2015 ዓ.ም የዓለም አቀፍ ስነ ተዋልዶ ጤና ስልጠና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል።

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የጽንስ እና ማህጸን ትምህርት ክፍል ውስጥም ከአምስት ዓመታት በላይ ሰርተዋል።

ዶክተር መቅደስ ዳባ በሀዋሳ የኒቨርሲቲ በህክምና ዶክትሬት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በህብረተሰብ ጤና ማግኘታቸውን ለምክር ቤቱ ዕጩ አደርገው ያቀረቧቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።

ቀጥሎም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጽንስ እና ማህጸን ሃኪም ሆነው ተመርቀዋል።

ከዚያም በኋላ በቅዱስ ጳውሎስ ሚለኒየም ሜዲካል ኮለጅ በቤተሰብ ምጣኔ እና ስነ ተዋልዶ ጤና ላይ አተኩረው ተምረዋል።

ባለትዳር እና የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ዶክትር መቅደስ የገዢው ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ አባል እንዳልሆኑ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጤናው ዘርፍ ባደረጉት አስተዋጽኦ ባሳዩት የላቀ ችሎታ እና ብቃትም ተመርጠው እንደሆነም ተናግረዋል።

Exit mobile version