Site icon ETHIO12.COM

የቶንሲል ህመም ምንነት

የቶንሲል በሽታ በጉሮሮ የኋላ ክፍል ላይ ያሉ ሁለት የጅምላ ቲሹዎች የሚከሰት ሆኖ በሕጻናት ላይ በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ህመሙ አንዴ ከያዘና በትክክል ሕክምና ካልተደረገለት በተደጋጋሚም ሊያጋጥም ይችላል።

ህመሙ በአብዛኛው ከሦስት ዓመት ጀምሮ ያሉትን ሕጻናት የሚያጠቃ ነው። በተለይ ዕድሜያቸው ከሦስት ዓመት እስከ 18 ዓመት ያሉ ሕጻናት እና ወጣቶች ከሁሉም በላይ ተጋላጭ ናቸው።

ከላይ ባሉ የዕድሜ ክልል ባሉ ህጻናት ላይ ቢብስም በየትኛውም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎችንም የሚያጠቃ ነው።

ይህ በሽታ በባክቴሪያ አሊያም በቫይረስ ሳቢያ ሊከሰት እንደሚችል የህክምና ባለሞያዎች ያስረዳሉ።

እነዚህ ቶንሲል እንዲከሰት የሚያደርጉ ባክቴሪያዎች ስትሬፕቶኮከስ (ስትሬፕ) ይባላሉ፡፡

ቫይረሶቹ ወይም ባክቴሪያዎቹ መተንፈሻ ቱቦዎ ውስጥ ገብተው ኢንፌክሽን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጀርሞችን በመፍጠር ለህመም ያጋልጣሉ።

ሰውነታችን ደግሞ ኢንፌክሽኑን ለመዋጋት ፀረ እንግዳ መከላከያ ይሠራል፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሰውነታችን ያመነጨው ፀረ እንደግዳ መከላከያ በቫይረሶች ይዋጥና እብጠት ይፈጠራል፡፡

በትምህርት ቤት የሚውሉ ህፃናት ከአቻዎቻቸው ጋር ያላቸው የቀረበ ግንኙነት/ንክኪ/ ለቫይረሶች እና ባክቴሪያዎች በቀላሉ እንዲጋለጡ ያደርጋችዋል ሲሉ የህክምና ባለሞያዎች ያስርዳሉ፡፡

እንደ ህክምና ባለሞያዎች ገለጻ ህመሙ አንድ ጊዜ ሊከሰት ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ደጋግሞ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል፡፡

በቅዝቃዜ ወቅት በቶንሲል መታመም የተለመደ ሲሆን፣ የቶንሲል ዓይነቶች በደረጃቸው ይመደባሉ፡፡

የቶንሲል በሽታ ምልክቶችን ስንመለከት ደግሞ ዋነኛ ምልክቶች የጉሮሮ ድርቀት እና እብጠት ሲሆን፣ አንዳንዴም በአፍ ለመተንፈስ እስከማስቸገር ሊያደርስ ይችላል፡፡ ተጨማሪ ምልክቶች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡-
*የጉሮሮ ሕመም
*ትኩሳት
*በጉሮሮ ላይ ቁስለት
*ራስ ምታት
*የምግብ ፍላጎት ማጣት
*የጆሮ ሕመም
*የአንገት ወይም የመንጋጋ ውስጥ እብጠት
*ትኩሳት እና ብርድ
*መጥፎ የአፍ ጠረን

በልጆች ላይ የሚታዩ የበሽታው ምልክቶች ደግሞ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡-
*የሆድ ህመም
*ማስመለስ
*መብላትም ሆነ መዋጥ አለመፈለግ

የቶንሲል ሕክምና
የቶንሲል ህመም ባህላዊ እና ዘመናዊ ህክምናዎች አሉት፡፡ ብዙ ግዜ ፈሳሽ በበቂ መጠን መውሰድ ምቾትን ሊሰጡ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ፣ እንደ ሾርባ ያሉ ትኩስ ፈሳሾች፣ የሞቀ ውሃ በማር እንዲሁም ቀዝቃዛ የሆኑ እንደ በረዶ ያሉ ነገሮች የጉሮሮ መከርከርን ሊያክሙ ይችላሉ፡፡ ጨዉ ባለው ውኃ አፍን መጉመጥመጥ የመሳሰሉ ነገሮች ቤት ውስጥ የሚደርጉ ህክምናዎቸ ቢኖሩም የህክምና ባለሞያዎች ግን በአፋጣኝ ወደ ህክምና ጣቢያ መሄድን ይመክራሉ፡፡

Via – EBC fb page

Exit mobile version