ሕንድ ውስጥ ከኮቪድ ያገገሙ ሰዎች ዓይነ ስውር በሚያደርግ ‘ብላክ ፈንገስ’ እየተጠቁ ነው

አሁን ደግሞ የሕክምና ባለሙያዎች ከኮቪድ-19 እያገገሙ ባሉና ባገገሙ ሕመምተኞች ላይ ‘ብላክ ፈንገስ’ የተባለ በሽታ እያዩ ነው። በሕክምና ቋንቋ ሙክሮሚኮሲስ የሚሰኘው ይህ በሽታ ሰው ለይቶ የሚያጠቃ ነው።

ብዙ ጊዜ ይህ በሽታ የሚመጣው ከአፈር፣ ዕፅዋት፣ የከብቶች ኩበት አሊያም ከበሰበሰ ፍራፍሬና አትክልት ነው። በሽታው ወደ ሰውነታችን አየር የሚገባባቸው ቀዳዳዎችን እንዲሁም ሳንባን በማጥቃት በተለይ ደግሞ ተደራቢ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ሊገድል ይችላል።

በተለምዶ የስኳር [ዳያቢቲስ] በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ የሰውነት የመከላከል አቅማቸው የደከመና የኤችአይቪና ካንሰር ተጠቂዎች በዚህ በሽታ የመሞት ዕድላቸው የሰፋ ነው።

ዶክቶሮች ይህ የመግደል አቅሙ 50 በመቶ የሆነ በሽታ የተስፋፋው በኮቪድ-19 እጅግ የታመሙ ሰዎች የሚወስዱትን ኃይል ሰጪ መድኃኒት ተከትሎ ነው ይላሉ።

ስቴሮይድስ አሊያም ደግሞ ሰው ሰራሽ ሆርሞን የሚባሉት ሳንባ እንዳይቆጣ በማድረግና የሰውነት መከላከል አቅምን በመጨመር ይታወቃሉ። ነገር ግን ዳያቢቲስ ያለባቸው እንዲሁም የለሌባቸው ሰዎችን የመከላከል አቅምን ሊያዳክሙም ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ነው ይህ ሙኮርሚኮሲስ የተሰኘው በሽታ የሚቀሰቀሰው ሲሉ ዶክተሮች ያብራራሉ።

በሁለተኛው ማዕበል እጅግ በተመታችው ሙምባይ ውስጥ ባሉ ሶስት ሆስፒታሎች የሚሠራው ዶክተር ናይር ከባለፈው ወር ጀምሮ ቢያንስ 40 ሰዎች በዚህ በሽታ ሲጠቁ ማየቱን ይናገራል።

ከባፈለው ታህሣሥ እስከ የካቲት ባለው ጊዜ በአምስት ዋና ዋና ከተሞች 58 ሰዎች በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል። አብዛኛዎቹ ሰዎች በዚህ የሚጠቁት ከኮቪድ-19 ካገገሙ በኋላ ከ12-15 ባሉት ቀናት ነው።


በአማራ ክልል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ መጠን ጨመረ- ሆስፒታሎችም ህሙማንን ማስተናገድ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አስታውቀዋል

ህሙማንን ለማስተናገድ እየተቸገርን ነው


የሙምባይ ሳዮን ሆስፒታል ባለፉት ሁለት ወራት 24 ሰዎች በዚህ ሰው ለይቶ በሚያጠቃ በሽታ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አስራአንዱ አንድ ዓይናቸውን እንዲያጡ ሲሆኑ ስድስቱ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በቤንጋሉሩ ከተማ የዓይን ቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ራንጉራጅ ባለፉት ሁለት ሳምንታት 19 በሙኮርሚኮሲስ የተጠቁ ሰዎች ማየታቸውንና አብዛናዎቹ ደግሞ ወጣቶች መሆናቸውን ይናገራሉ።

ዶክተሮች ይህ በፈንገስ የሚመጣው በሽታ በሁለተኛው ማዕበል እንዲህ በፍጥነት መስፋፋቱ እንዳስደገነጣቸው ይናገራሉ። ዶ/ር ናይር ባፈለው አንድ ዓመት ሙምባይ ውስጥ 10 በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ማግኘቱን ያስታውሳል። ነገር ግን በዚህ ዓመት እጅግ በፍጥነት መስፋፋቱን ይናገራል።

በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች አፍንጫቸው ይታፈናል፣ ይደማል እንዲሁም ዓይናቸው አካባቢ እብጠት ሕመም ይሰማቸዋል። ትንሽ ቆይቶ የማየት አቅማቸው እየተዳከመ ይመጣና በስተመጨረሻ ዓይነ ስውር ይሆናሉ። ይህን በሽታ ለመከላከል የሚረዳው መድኃኒት አንዱ 48 ዶላር የሚሸጥ ሲሆን ይህን መድኃኒት ለተከታታይ ስምንታት መውሰድ ግድ ይላል።

via – bbc amharic

 • በኢትዮጵያ ፀሐይ ያጠላው ጥቁር ደመና
  ” በጥቅሉ፣ ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበት ሕግ የማስከበር ተልዕኮ፣ በውጭ ኃይሎች ጫና የተራዘመ ቢመስልም በአጠረ ጊዜ መፍትኄ ያገኛል፡፡ በሉዓላዊ መንግሥቷና በሕዝቧ ሙሉ ዐቅም የውስጥ ችግሯንም ትፈታለች፡፡ በኢትዮጵያ ፀሐይ ላይ ያጠላው ደመናም ይገፈፋል፡፡ …. ጽሑፌን በአንድ መጠየቅ መቋጨት ወድጃለሁ፡– ለመሆኑ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ተቃቅራ፣ ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር በመወገኗ የምታገኘው ጥቅም ምንድነው? Banana republic?” ነጻ አስተያየት ቹቹ አለባቸው –…
 • የሰሜኑ ጦርነትና የመላ ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነት !   እስክንድር ነጋ! ቂልንጦ አዲስ አበባ
  ነጻ – አስተያየት 1.1 —ረሃብ ወደ መሥራቱ መሸጋገር በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለው ጦርነት ያለ ምክንያት የዓለም አቀፉን ማበረሰብ ትኩረት አልሳበም፡፡ ሶስትና አራት ከባድ ከበድ ከበድ ያሉ ምክንያቶች አሉ ።ግን እንዳቸውም ከአንዣበበው ረሃብ በላይ አይደሉም፡፡ ልብ እንበል፡፡ ያንዣበበው አደጋ ድርቅ አይደለም፡፡ ዘንድሮ የዝናብ ችግር የለም፡፡ ድርቅ የሌለበት ረሃብ ነው ያንዣበበው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ረሃብ፣ “ሰው ሰራሽ ረሃብ”…
 • የጀግናው ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ቆመ
  በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የጀግናው ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ቆመ። ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2014 የቆመው የጀግናው ሐውልት ያረፈበት ስፍራ ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ በመባል ይታወቃል። ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ማንናቸው? …በዚህ ጊዜ ከጠላት ወገን በተተኮሰ አየር መቃወሚያ የሚያበረው ኤፍ 5 ኢ ተዋጊጀት ተመታ፡፡ ይኼኔ እሱ በዥንጥላ ወርዶ ህይወቱን ማትረፍ ነበረበት፡፡ ነገርግን የሚያበረውንም…
 • “ጭፍራ ከተማና ሰላማዊ ዜጎች በከባድ መሳሪያ እየተደበደቡ ነው” አፋር ክልል
  ጭፍራ ከተማን ለማውደም ትህነግ ከባድ መሳሪያ እያዘበ እንደሆነ፣ ድብደባው የታጠቀውን ሃይል ሳይሆን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑና የዘር ማጥፋት ተግባር እንደሆነ የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት አመለከተ። የትግርያ ሕዝብ ነጻ አውጪ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም። ሙሉ በሙሉ ከታች ያለውን ያንብቡ። ጁንታው ሰላማዊ ዜጎችን ታርጌት ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በጭፍራ እያደረገ ነው! አሸባሪው ህወሀት በአፋር…

Leave a Reply

%d bloggers like this: