Site icon ETHIO12.COM

በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋረጠ



የጁንታው ርዝራዦች አዲጉዶም በተባለ አካባቢ ከአላማጣ – መሆኒ – መቐለ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባደረሱት ጥቃት በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።

ከዚህ ቀደም መስመሩ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበረና ለመጠገንም ረዘም ያለ ጊዜ እንደወሰደ የገለጸው ተቋሙ፣ ክልሉ ኃይል ከሚያገኝባቸው መስመሮች አንዱ የአላማጣ – መሆኒ – መቐለ መስመር ሲሆን የተከዜ አክሱም መስመር የጥገና ሥራው እየተከናወነ እንደነበር መገለፁ አይዘነጋም ተብሏል።፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የወደመውን መሰረተ ልማት ዳግም በመጠገን መልሶ ኃይል ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ያገኘነውን መረጃ ያመለክታል።
(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version