Site icon ETHIO12.COM

አብነት ገብረመስቀል ከኮቪድ አገግመው ወደ ቢሮ ተመለሱ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤትና ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ አዲስ በሰጡት ሹመት የሚድሮክን ዋና ስራ አስፈፃሚነ የሆኑት አቶ አብነት ገብረመስቀልን ከኮቪድ በጠና ታመው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ማገገማቸው ተገለጸ።

ከሚስዶክ በተጨማሪ በኮንስክትራክሽን፣ በሆቴሎች እና በሪል ስቴት ዘርፍ ያሉትን ኩባንያዎች በሙሉ እንዲመሩና ፋርማኪዩርን እየመሩ እንዲቀጥሉ ስልጣን የተሰጣቸው አቶ አብነት የታመሙት በኮቪድ 19 ቫይረስ ተያዘው ነበር። የሸራተን ዜና አቀባያችን እንዳሉን አቶ አብነት በጸና ታመው ነበር። መተንፈስ ተስኗቸው የከፋ ደረጃ በመድረሳቸው ቤተሰቦቻቸውና የሚወዷቸው እጅግ ተደናግጠው ሰንብተው ነበር።

በሸራተን ሆቴል አንድ ክፍል ውስጥ በመተንፈሻ መሳሪያ እገዛና እጅግ ጥብቅ ክትትል እየተደረገላቸው ያገገሙት አቶ አብነት አሁን እዛው ሸራተን ታለው ቢሯቸው ስራቸውን መስራት መጀመራቸውን የዜናው ምንጭ አስታውቀዋል።

” ደንግጠን ነበር” ያሉት ወዳጃቸው እንደነገሩን ሁሉም አልፎ ዛሬ እጅግ በመልካም ሁኔታ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። አቶ አብነት ሸራተን ውስጥ በልዩ ክብካቤ ሲታከሙ መቆየታቸው በድብቅ የተያዘ ቢሆንም ሰራተኞች መረጃ ደርሷቸው እንደነበር ኢትዮ12 አረጋግጣለች። ወዳጃቸው አክለው አቶ አብነት በጠና መታመማቸውን የሰሙና ስጋት ገብቷቸው የነበሩ ወገኖችና በጸሎት ሲተጉ ለነበሩ ክፍሎች ትልቅ ዜና እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ አብነት ደምሰው ለማ ወይም በተለምዶ አራዊት ጤናው በመታወኩ ወገን ወዳዶች ወደ አገር ቤት እንዲመለስ ለማድረግ የሳቸውን ፈቃድ ለመጠየቅ መዘጋጀታቸውን ጠቅሰን ዜና መስራታችን የሚታወስ ነው።

ፎቶ ካፒታል ጋዜጣ የሸገር ዳቦ ፕሮጀክት ምርቃት ወቅት የተነሳ


Latest stories

Exit mobile version