Site icon ETHIO12.COM

በትግራይ አምስት ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት ጀመሩ፣ አንዱ ኤክስፖርት ጀምሯል

የመልሶ ማቋቋሙ አንድ አካል የሆነው ስራ በስኬት እየተከናወነ መሆኑንን ከሚያመልክቱት ተጋሮች አንዱ የፋብሪካዎች መልሶ ስራ ማስጀመር መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም በትግራይ አምስት ፋብሪካዎች ስራ መጀመራቸውና አንደናው ደግሞ ኤክስፖርት መጀመሩ ተመልክቷል።  ይህ የተገለጸው በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰብሳቢነት የሚመራው የብሄራዊ ድንገተኛ አደጋ አስተባባሪ ማዕከል የሚኒስትሮች ኮሚቴ ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄድበት ወቅት ነው።

በስበሰባው የኮሚቴው አባል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በትግራይ ክልል እና በመተከል ዞን በማድረግ ላይ ስላሉት የአስቸኳይ እርዳታ አቅርቦትና ስርጭት ሚኒስትሯ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ እያቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከጊዜያዊ የእርዳታ አቅርቦት ባሻገር ህዝቡን በቋሚነት መልሶ የማቋቋምና ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ስራ በተጓዳኝ እየተካሄደ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች የዕርዳታ ስርጭቱና ክፍፍሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ መምጣቱን አረጋግጠዋል፡፡  በክልሉ ያለው አጠቃላይ ሁኔታም እየተሻሻለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት አምስት ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ስራ መጀመራቸውን እና ከእነዚህ አምስት ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ ለውጭ ገበያ አቅርቦት መጀመሩን መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዝግጅት ክፍላችን ያናገራቸው የትግራይ ተወላጆች እንዳሉት አሁን መርጋጋትና ነገሮች ወደነበሩበት እየተመለሱ ነው። ዋናው ችግሩ የሚዲያው ፕሮፓጋንዳ ነው ብለዋል። አያይዘውም እርቅ ላይ ቢተኮር እንደሚሻል ጠቁመዋል።

Exit mobile version