ETHIO12.COM

የመቀሌው የአምነስቲ ወኪል በሰሜን ዕዝ የመከለከያ ሰራዊት አባላት ላይ ዳግም ክህደት ፈጸመ!! ወታደረ ሰብአዊ መብት የለውም!!

የአምነስቲ የምስራቅ አፍሪቃ ወኪል፣ ተመራማሪ፣ አጥኚ … ያሻችሁን በሉት ትናት ቪኦኤ ላይ ቀርቦ ወታደር የሰባዊ መብቱ ተጣሰ በሚል በልዩ ሁኔታ የሚመረመርበት አግባብ እንደሌለ ሲናገር ሰማሁት። ከምርኮ በሁዋላ በአያያዝ ችግር ካለ እንጂ ከዛ ውጭ ያለ ጉዳይ በሰብአዊ መብት ጥሰት እንደማይታይ አስረዳ። ታግተው መኪና ላያቸው ላይ የተነዳባቸው። ልብሳቸው ወልቆ እርቃናቸውን የተረሸኑ፣ በጅምላ የታረዱ … ዝም ከምል ብዬ ይህን አልኩ።

የትግራይ ህዝብ ሁለት ነው። አንዱ ተረጂ፣ ሌላው ተተቃሚ። ተረጂው ስንዴ የሚሰፈርለት፣ ትህነግ ከሌለ ስንዴ የሚያገኝ የማይመስለው። ሌላኛው የስብሃት ስርወ መንግስትን ተጠግቶ ወይም እዛ ቀለበት ውስጥ ተቀትሮ እያገለገለ የሚኖር። እነዚህ ሁለት ክፍሎች ትህነግን የመቃወም አቅም የላቸውም። ምክንያቱም የተተከሉት ስንዴና ደሞዝ ላይ በመሆኑ። የተቀሩት ሚሊየኖሮቹ የገዢ መደቦች ናቸው ይመለካሉ።

ለአምነስቲ ፍስሃ ተክሌ – ከእሸቴ ሞገስ

Fisseha Tekle

ሰሞኑን አብይ አሕመድ ፓርላማ ተገኝተው የሰጡት ምላሽ። ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከመጡ ወዲህ ካደረጓቸው ንግግሮች ሁሉ እጅግ አነጋጋሪና የአብዛኞችን ልብ የነካም ነበር። በኩርፊያ የጥላቻ ጥግ ተወሸቀው መርዝ ከሚረጩት፣ እየተከፈላቸው ሽብር ከሚነዙት እፉኝቶች፣ እንዲሁም ፍላጎታቸው በግልጽ የማይታወቅ የሚዲያ ባለቤቶች ካልሆኑ በቀር የአብይ ንግግር በዜጎች ዋጋ አግኝቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም።

እንደ መሪም እጅግ የሚገርም ጸዳል ተላብሰውና በመሪነት ሞገስ የሚመሩትን ሕዝብ አክብረው ስለ ህሊና፣ ሞራልና ልዕልና ያቀረቡት ንግግር አገር ወዳድ ለሆኑ ሁሉ ልብን የሚያርስ፣ ምን አልባትም ወደፊት ታሪክ ሊሆን የሚችል እንደሆነ አስተያየት የሰጡ አሉ።

ኢትዮጵያን “ ኪዳን ያላት” ሲሉ ሁሉም በእምነቱ የሚኮራባት አገር እንደሆነች አስረድተው ሲያበቁ “ የሚያግዘን እንፈልጋለን፤ ለመታገዝ ግን ክብራችንን መጣል አይጠበቅብንም፤ በከርሱ ተደልሎ እጁን የሚጠመዘዝ ተላላኪ መንግስት አይኖርም፤ አታስቡት …” ሲሉ ንግግራቸው ትንፋሽን የሚሰርቅ ነበር። በተለይም ተላላኪው ህወሃትና መሪው መለስ ትውልዱን እንዴት እንዳመከኑት ለሚረዱ ዜጎች፣ የዚህ ቁጭት ለሚለበልባቸው አገር ወዳዶች፣ የአብይ ንግግር ዝም ብሎ ለንግግር ፍጆታ የተባለ ሳይሆን ሁሉም ዜጋ ልጆቹ ላይ እንዲሰራ የሚያሳስብ፣ የቀደመውን ጭንጋፍ ዘር የሚያመክን ጭምር ነበር። እንደወርቅ የጎላው ግን ” ብቻችንን እናልፈዋለን” ያሉት ባለ ብዙ ዘርፍ ንግግር ነው። እሳቸው እንዳሉት ኢትዮጵያ ዛሬ ብቻ ሳይሆን በርካታ ጊዜያት ተጥላና ተክዳ ነበር። ግን አልፋለች።

ትህነግ የኢትዮጵያን ልጆች በለሊት በተኙበት ጨፍጭፎ፣ አግቶና የአገሪቱን መሳሪያ ሰማኒያ በመቶ ዘርፎ፣ 200 ሺህ ሰራዊት ገንብቶ እንዳሻው መናኘት ያልቻለው ኢትዮጵያ የሚያልፉና የሚያሳልፉ ጀግኖች ስላሉዋት ነው። ይህቺ በየዘመኑ አሻጋሪ የማይነጥፋባት ኢትዮጵያ ዛሬም የተቃጣባትን ሁሉ አልፋ እንደምትሻገር የሁሉም ዜጋ እመነት ነው።

ይህን እውነት ታላቅ ሞገስ ውስጥ ሆነው ሲያስረዱ ቁጭት እየለበለባቸው “ ክህደት ተፈጽሞብን፣ ግፍ ተፈጽሞብን፣ ተገለን፣ ተዘርፈን፣ …. ስናበቃ ” በማለት በውዱና ተተኪ በሌለው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ግፍ ለነጮቹ አልቃሾቹ ስለምን ይህን አሰቃቂ ወንጀል “ግፍ ሊሉት አልቻሉም?” በሚል ጥያቄ አቅርበው ነው። ለጥያቄውም ከበረዶ የነጻ መልስ በመስጠት ነው።

ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ትህነግ የኢትዮጵያን ካባ ለብሶ በዓለም አቀፍ ተቋማት፣ እንደ አምነስቲ ባሉ ተከፋይ ድርጅቶች፣ የራሱን ሰዎች ሲሰገስግ መኖሩን ነው የነገሩን። እሳቸው ይህንን ባይሉም በተደጋጋሚ በማስረጃ ሲባል እንደነበረው ትህነግ ከኢትዮጵያ የዘረፈውን ገንዘብ በመርጨት ሎቢስት ቀጥሮ፣ ዲፕሎማቶችን ደልሎ፣ ሚዲያዎችን አስክሮ እንዳሻው የሚጋልባቸው ነጭ አጋሰሶች ተጠቅሞ ዓለም አስቷል።

ትህነግ ኢትዮጵያን በኢትዮጵያ ሃብት እየለበለበ መኖሩ ሃቅ ሲያብራሩ የሙቀጫና ዘነዘና ምስላ የተጠቀሙት አብይ አሕመድ፣ ዘነዘና እናቱን ከልደበደበ፣ ካላሰቃየ ስራ የሰራ እንደማይመስለው ሁሉ ትህነግም ኢትዮጵያን ካላዋረደ፣ ካልዘረፈ፣ ዝቅ ካላደረገ፣ ካልሸረበባትና ሊቸረችራት ካላሴረባት ስራ የሰራ እንደማይመስለው ሲያስረዱ መገረም ያልፈጠሩት ለሙቀጫዋ ልጆች ብቻ ነው።

ኢትዮጵያን በስሟ ለመጥራት የሚጠየፋት መለስ በድንገት ለአስታማሚ እንኳን ሳይደርስ መስፋንጠሩ የዚሁ ባለኪዳን የሆነው ሕዝብ ጸሎት ስለመሆኑ ዛሬ እንደ አዲስ እየተሰበከ ባለበት ወቅት፣ በየቦታው የተወተፉት ዘነዘናዎች ሲወራጩ ማየት አያስገርምም።

የምስራቅ አፍሪቃ የአምነስቲ ተወካይ ፍስሃ ተክሌ ትህነግ በየቦታው ከወሸቃቸው እናታቸውን ሲቀጠቅጡና ሲያዝሉ ከሚውሉ ዘነዘናዎች አንዱ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል። እሱም አይክደውም። ትናት በቪኦኤ ቀርቦ “የፌስ ቡክ ወሬ” ሲል ጁንታው የቀረጸው ዘነዘና መሆኑንን ሊያስተባብል ሞክሯል።

ቪኦኤ ባሰራጨው ዜና በስመ ማመጣጠኛ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሊያስተባብል የተጋበዘው ይህ የጁንታው ዘነዘና፣ ከመቀሌ ተመልምሎ አምነስቲ እንዴገባ መደረጉ ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ “ ትህነግን አላውቀውም” አይነት ምህላ አሰምቷል።

በወጉም ባይሆን፣ ራሱን ችሎ ተከራካሪ ሊቆምለት የሚገባ ሆኖ ጉዳይ ሆኖ ሳለ፣ የሽፍጡና ቁማሩ ቁልፍ ያለው እዚሁ ጉዳይ ላይ ቢሆንም፣ ግፍ የተፈጸመባቸው በተኙበት ታርደው፣ በተኙበት ተረሽነው፣ አስከሬናቸው እንኳን ክብር አጥቶ ልብሳቸውን አውልቀው ራቁታቸውን ለአውሬ እንደሰጧቸው በገሃድ ታይቶ፣ ከትግራይ ልጆች የወለዷቸው ልጆች ባንዳ እየተባሉ ሲበለቱ ለመበለታቸው በቂ ምስክር እያለ፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮች ጫማቸውን አውልቀው እንደ ሌባና ወራሪ በባዶ እግራቸው ሲያሰቃዩዋቸው በገሃድ ለጀበድ በሚል በተቀረጸ ምስል እየታየ፣ በስለፍ ባዶ እግራቸውን የሚሄዱትን ትጥቅ የሌላቸውን ወታደሮች በሲኖ ትራክ ጭነት መኪና ሲጨፈልቋቸው፣ አጥንታቸውን ሲያደቋቸው … ይህ ሁሉ ሲሆን ያዩ፣ የነበሩ፣ የተረፉ፣ አምላክ ለምስክርነት ያበቃቸው እያሉ አምነስቲም ሌሎችም ዝም አሉ።

ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ አንዱና ዋናው ምክንያትም ይህ ነው። ይህ ኬናያ ናይሮቢ ተቀምጦ ለትህነግ የሚጫወተው ባንዳ፣ “ ወታደር በሰብአዊ መብት ጉዳዩ አይታይም” ሲል እንደ ዱቄት በኖ ለተበተነው አረመኔ ድርጅቱ ጥብቅና ቆመ። አይኑን በጨው ታጥቦ አምነስቲ ከመርኮ በሁዋላ ስለሚፈጸም የመብት ጥሰት እንጂ በውጊያ ላይ ስለሚፈጸም ጉዳይ እንደማያገባው አስታወቀ። ዳሩ ምን ያደርጋል ከዝንጀሮ ቆንጆ እንዲሉ ወይ አዋቂ አልጠየቀው፣ ወይ አውቆ አልመለሰ እንዲሁ ጠያቂም መላሽም አዝጦንኛ አውርተው ዝግጅቱ አለቀ።

“ ሰራዊቱ እኮ ተኝቶ ባለበት ነው የተመታው ይባላል” ለሚለው ጥያቄ መስል ጥያቄ “ ለእሱ ማስረጃ የለም” ያለው የመቀሌው ጁንታ ፍስሃ፣ ማይካድራ ላይ ህዝብ አርደው የሸሹ የሳምሪ አባላትን ጠይቆ ፍርደ ገምድል ሪፖርቱን ሲሰራ ግን ምስክርና ማስረጃ ነበረው። ወይም እነሱን እንደማስረጃ ለመቀበል አላመነታም። ምክንያቱም የጁንታውን ዘነዘና የዋጠ፣ ባንዳ ነውና። የማስረጃ ፍረጃውን አስመልክቶ መመዘናውን ቢያንስ ለግንዛቤ አብራራ አልተባለምና የክህደት መርዙን ጢቅ አደረገብን።

እንደ ፍስሃ አይነት ህሊናው የዶለዶመ በእንዲህ ያለው ቅዱስ ስራ ውስጥ መሳተፉ ቢያሳዝንም አያስገርምም። የሚያበሳጨው ግን በስመ ማመጠጠኛ የሰራዊቱን ስም እያነሱ ቁስላችንን የሚነካኩን አስመሳዮች ጉዳይ ነው። ታፍነው የነበሩ ጀነራሎች አልሞቱም አሉ። ከተኙበት ተይዘው ተወስደው የተረሸኑ ስለመኖራቸው ጥሻ ውስጥ ገብተውና ሚስቶቻቸው ደብቀዋቸው የተረፉ ምስክሮች አሉ። በመኪና ላያቸው ላይ ሄደውባቸው አካላቸው ደቆ ለታሪክ የተረፉ ግማሽ ሰዎች አሉ። በጅምላ ሲረሸኑና ዛሬ ድረስ በሃዘኑ ድንጋጤ እየባነኑ ያሉ አሉ… ለአቶ ተክሌ ልጅ ይህ አይታየውም። ለምን አይኑና ልቡ ላይ የተተከለው ዘነዝና የማያስብ ቆሞ ቀር አድርጎታል።ከርሱንና የከርሱን ምንጭ ትህነግን አምላኩ አድርጎ ዋናውን የፈጣሪ ልዕልና ክዷል። የአስተሳሰብ ሚዛኑ በከርሱ አማካይነት ልምሻ ስለያዘው ደም አዙሮ ጫካ ለቀረቅረው አውሬ ብቻውን እንደ ቁራ ይጮሃል። በደም ታጥቦና በንጹሃን ነብስ ህሊናው ለሸተተው ትህነግ መከታ ለመሆን ይንፈራገጣል። በዚህ ቁመናው “ ለምን ተተቸሁ” ሲል “አሳፋሪ” ለማለት ይሞክራል። እንደው ለመሆኑ ትህንግ ሰፈር ምን የሚሉት ሃፍረት ኖሮ ያውቃል?

የትህነግ አውሬዎች ባደባባይ ህጻናትን ሲደፍሩ የአቶ ተክሌ ልጅ የት ነበርክ? የተወለድከብት ከተማ እህቶችህ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ ለመሆኑ ዜናውን እንኳን ታነብ ነበር? ብዙ ላነሳልህ አስቤ “ ዘነዘና” የዋጥክ የትህነግ አንድ አካሉ ወይም ዋናው ብልቱ፣ ቅንዝሩ፣ መሲሰኛው ነህና መቼ ይገባሃል!! ተውኩት

እስኪ በሚል የቲውተር ገጽህን ይህንን ጽሁፍ ከመሳፌ በፊት ጎበኝቼልህ ነበር። ወቀሳውና ሃሜቱ ትክክል መሆኑንን ከማረጋገጥ ውጭ ምንም አዲስ ነገር አላገነሁም። ግን የማልደብቅህ ነገር ቢኖር ተሳስቼ የጌታቸው ረዳ ገጽ የገባሁ መስሎኝ ስምህን ደግሜ አይቻለሁ። እሱም ያንተው ቢጤ ዘነዘና ነው ለማለት ነው። ደግነቱ የጀግኖች እናት ኢትዮጵያ ዛሬ ከዘነዘናዎች ራሷን አላቃ በቴክኖሎጂና በሮቦት መስራት ጀምራለች። አንድንድ የዘነዘናው ስንጣሪዎች እዛና እዚህ እያሉ ቢያውኩም ይታለፋል። ምክንያቱም “ ኪዳን አለን” !!

የትግራይ ህዝብ ሁለት ነው። አንዱ ተረጂ፣ ሌላው ተተቃሚ። ተረጂው ስንዴ የሚሰፈርለት፣ ትህነግ ከሌለ ስንዴ የሚያገኝ የማይመስለው። ሌላኛው የስብሃት ስርወ መንግስትን ተጠግቶ ወይም እዛ ቀለበት ውስጥ ተቀትሮ እያገለገለ የሚኖር። እነዚህ ሁለት ክፍሎች ትህነግን የመቃወም አቅም የላቸውም። ምክንያቱም የተተከሉት ስንዴና ደሞዝ ላይ በመሆኑ። የተቀሩት ሚሊየኖሮቹ የገዢ መደቦች ናቸው ይመለካሉ።

የአቶ ተክሌ ልጅ ተተቃሚ ነህ። ተተቃሚነትህ በጩኸትህ መጠን ወደጎን የስጋ ዘመዶችህ ዘንድ ይደርሳል። ይህ ጥቅም ሲቀር በየሚዲያው ብታላዝን፣ ነብሰ ገዳዮችን ሱዳን ደውለህ ምስክር አድርገህ ሪፖርት ብታዘጋጅ አያስገርምም። የምን ምስክር ዲምቢጥ ነውና !!
Exit mobile version