Site icon ETHIO12.COM

የአርተፊሻል ደመናው ነገርስ?

artificial rain

Belay Bayisa

ግብፅ “ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ መጠን በሳተላይት እንዳላይ ሆን ብላ አከባቢው በአርተፊሻል ደመና እንዲሸፈን አድርጋብኛለች” ብላ የመክሰሷ ነገርስ?

ባሻዬ – የዝናቡ ሲገርምህ ደመናውን ጨመረልህ?

በእርግጥ የህዳሴው ግድብ ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ባሻገር ለኛ ለኢትዮጵያውያን፦

ታሪክ ነው – የአሁኑ ትውልድ አሻራ

ዳግማዊ አድዋ ነው – መዘከርያ

የመደራደርያና ተፅዕኖ መፍጠሪያ አቅማችን ነው

የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካን ገፅታ የሚቀይር ስለመሆኑ

በቀጠናው ብሎም በዓለም ደረጃ ለምን ያወዛግባል ሲባል በጥቅሉ የሃይድሮ-ፓለቲካ ሲሆን በተለይ ደግሞ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ እንዲሁም የኢትዮጵያን እድገት ስለሚያፋጥነው ነው።

በራስ ጥሪት እና በራስ ጥረት የማደግ ምልክት እና መተማመኛ ነው

የመስኖ ልማትን ማስፋፊያ እና ምርታማነትን መጨመር የሚያስችል ነው።

ስራ አጥነት ለመቀነስ እና ስራ ፈጠራን ያበረታታል ብሎም ኢንቨስትመንትን ያበረታታል፤ ያጠናክራል።

ለአፍሪካ ብሎም ለጥቁር ህዝቦች የእድገት ተምሳሌት፣ ምልክትና ኩራት ጭምር ነው

አንድነታችንን የምናጠነክርበት የጋራ ሃብታችን እና ጠላትን መመከቻ ኒውክለር ትጥቃችን ጭምር ነው።

ከተፋሰሱ ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን ያጠናክራል። በተለይ ግብፅና ሱዳንን በእጅጉ ይጠቅማል።

የውሃውን ፍሰት ማኔጅመንቱን የተመጠነ ያደርገዋል።

የአከባቢ ጥበቃ ስራን ያጠናክራልይህን እና ሌሎች ያልጠቀስኳቸውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ስላለው የዓለም አይን ግድቡ ላይ ነው። ግብፅ ደግሞ የውስጥ ፓለቲካዋን ጭምር የምታስተነፍስበት መሳርያዋ ስለነበር እርሱም ሊቀርባት ነው። ማንኛው ጫና እና ፈተና ጥቅምን መሰረት ያደረገ ነው።በአጠቃላይ ገብፅ በብቸኝነት መጠቀምን እንጂ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሰብ አትፈልግም። ላሚቷን ሳትቀልብ ወተት የምትፈልግ ደፋር ነች። በላይ ባይሳመጋቢት 20/2013 ዓ.ም


Exit mobile version