ETHIO12.COM

የያሬድ ጥበቡ ጥንካሬ ህወሃትን (ሙት) አምላኪነቱ ብቻ!!

አቶ ያሬድ የቀረው “መለስ ይመለሳል፤ ፃድቃን ያፀድቃል” ማለት ብቻ ነው 

የያሬድ ጥበቡ ነገር

ብአዴን የተሰኘው ድርጅት በድን ሆኖ የኖረው ከአፈጣጠሩ ጀምሮ እንደ እስስት ተለዋዋጭ ባህሪ ባላቸው እንደ ያሬድ ጥበቡ( Yared Tibebu) አይነት ሰዎች በመመራቱ ይመስለኛል። አቶ ያሬድ ህወሓትን ከማምለኩ ውጪ በምንም ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም ኖሮት አያውቅም። ዛሬ ያንቆለጳጰሰውን ነገ ተነስቶ ያለበቂ ምክንያት ሲቃወመው ታያለህ። ዝም ብሎ በነዱት ነው የሚነዳው።

(እንደ እኔ እንደ እኔ በየጊዜው አቋማቸውን የሚቀያይሩ ግልብ ሰዎች ሲያጋጥሙን እንደ ወንዝ ሳይሆን “እንደ ያሬድ ነው የሚነዱት” ብንል ሁላችንም ሊያግባባን የሚችል አገላለፅ ይሆናል ብየ አስባለሁ 

ይህ ግለሰብ ከህወሓት አሽከርነቱ ተላቆ አሜሪካ መኖር ከጀመረ በርካታ አመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁንም ድረስ ሞቶ የተቀበረውን ድርጅት ከማምለክ አልተመለሰም። በአንድ ወቅት “በረከት ስምኦን እና አዲሱ ለገሰ እንደ እንጀራ ይርቡኛል፤ እንደ ውሃ ይጠሙኛል” ብሎ ጉድ እንዳላስባለን አሁን ደግሞ ” ፃድቃን ገብረ ተንሳይ የአዲሱ የትግራይ ሰራዊት መሪ ሆኖ መምጣቱ በትግራይ ተስፋ እንዳልቆርጥ ያደርገኛል” ሲል እያስደመመን ይገኛል። ከወረዱ አይቀር እንደዚህ ነው።

ያሬድ እና መሰሎቹ ከሚፈፅሙት ድርጊት የተረዳሁት አንድ ነገር የወያኔ አሽከር ሆኖ ያገለገለ ግለሰብ በአካል ነፃ ቢወጣም አዕምሮው መቼም ቢሆን ከባርነት መላቀቅ የማይችል መሆኑን ነው። ለዚህም ይመስለኛል በመጦሪያ እድሜያቸው በረሃ የገቡት የቀድሞ ጌቶቹ ተአምር ይሰራሉ ብሎ ያመነው። አሁን እኮ አቶ ያሬድ የቀረው “መለስ ይመለሳል፤ ፃድቃን ያፀድቃል” ማለት ብቻ ነው 

ከሃይሌ ሙሉ ፌስ ቡክ የተወሰደ


Exit mobile version