የያሬድ ጥበቡ ነገር
ብአዴን የተሰኘው ድርጅት በድን ሆኖ የኖረው ከአፈጣጠሩ ጀምሮ እንደ እስስት ተለዋዋጭ ባህሪ ባላቸው እንደ ያሬድ ጥበቡ( Yared Tibebu) አይነት ሰዎች በመመራቱ ይመስለኛል። አቶ ያሬድ ህወሓትን ከማምለኩ ውጪ በምንም ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም ኖሮት አያውቅም። ዛሬ ያንቆለጳጰሰውን ነገ ተነስቶ ያለበቂ ምክንያት ሲቃወመው ታያለህ። ዝም ብሎ በነዱት ነው የሚነዳው።
(እንደ እኔ እንደ እኔ በየጊዜው አቋማቸውን የሚቀያይሩ ግልብ ሰዎች ሲያጋጥሙን እንደ ወንዝ ሳይሆን “እንደ ያሬድ ነው የሚነዱት” ብንል ሁላችንም ሊያግባባን የሚችል አገላለፅ ይሆናል ብየ አስባለሁ
ይህ ግለሰብ ከህወሓት አሽከርነቱ ተላቆ አሜሪካ መኖር ከጀመረ በርካታ አመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁንም ድረስ ሞቶ የተቀበረውን ድርጅት ከማምለክ አልተመለሰም። በአንድ ወቅት “በረከት ስምኦን እና አዲሱ ለገሰ እንደ እንጀራ ይርቡኛል፤ እንደ ውሃ ይጠሙኛል” ብሎ ጉድ እንዳላስባለን አሁን ደግሞ ” ፃድቃን ገብረ ተንሳይ የአዲሱ የትግራይ ሰራዊት መሪ ሆኖ መምጣቱ በትግራይ ተስፋ እንዳልቆርጥ ያደርገኛል” ሲል እያስደመመን ይገኛል። ከወረዱ አይቀር እንደዚህ ነው።
ያሬድ እና መሰሎቹ ከሚፈፅሙት ድርጊት የተረዳሁት አንድ ነገር የወያኔ አሽከር ሆኖ ያገለገለ ግለሰብ በአካል ነፃ ቢወጣም አዕምሮው መቼም ቢሆን ከባርነት መላቀቅ የማይችል መሆኑን ነው። ለዚህም ይመስለኛል በመጦሪያ እድሜያቸው በረሃ የገቡት የቀድሞ ጌቶቹ ተአምር ይሰራሉ ብሎ ያመነው። አሁን እኮ አቶ ያሬድ የቀረው “መለስ ይመለሳል፤ ፃድቃን ያፀድቃል” ማለት ብቻ ነው
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል