በትግራይ ክልል ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ከአንድ ሚሊየን የሚበልጡ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አምስተኛው ምዕራፍ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ።
የልማታዊ ሴፍቲኔት የአምስተኛ ምዕራፍ መረሃ ግብር በክልሉ ለመጀመር የሚያስችል የትውውቅ መድረክ ዛሬ በመቀሌ ከተማ ተካሄዷል።የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ያስሚን ወሃብረቢ ÷አምስተኛው ምዕራፍ በትግራይ ክልል የሚጀመረው ህዝቡን ካለበት ችግር እንዲወጣ ለማስቻል ታቅዶ የሚካሄድ ነው።
ይህም ክልሉ ወቅታዊ ችግር ባለበት ሁኔታ የሚጀመር ቢሆንም ያለው ክፍተት ለመሙላት ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።ፕሮግራሙ በክልሉ 55 ወረዳዎች ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊየን ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለሚካሄደው የሴፍቲኔት ፕሮግራም 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መመደቡን ሚኒስቴር ዴኤታዋ አስታውቀዋል።በሴፍቲኔት ፕሮግራሙ የሚታቀፉ ዜጎች በተፈጥሮ ሃብትና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች በማሳተፍ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ የተዘጋጀ ዕቅድና ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚቆይ መሆኑን አስረድተዋል።
የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሳኒ ረዲ በበኩላቸው÷ በሀገሪቱ ቀደም ባሉት ዓመታት በፕሮግራሙ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ በተካሄዱ ስራዎች የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭነትን በመቀነስ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።በዚህም በተለያዩ ወቅቶች በሀገሪቱ ይከሰት የነበረውን ድርቅ ለመቋቋም ማስቻሉን ተናግረዋል።በኢትዮጵያ ባለፉት አራት ምዕራፎች በፕሮግራሙ ከታቀፉት ወገኖች ሶስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚሆኑት የምግብ ዋስትና በማረጋገጣቸው ተመርቀው መውጣታቸው ሚኒስትር ዴኤታው አመልክተዋል።
አምስት ሚሊየን በሚጠጋ ህዝብና በተወሰኑ ወረዳዎች ሲካሄድ የቆየው ይሄው ፕሮግራም በአሁኑ ወቅት እየሰፋ መምጣቱን አስረድተዋል።የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገብረህይወት÷ ክልሉ ከደረሰበት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማውጣት በሚደረገው ጥረት የፕሮግራሙ መጀመር የሚደገፍ መሆኑን ተናግረዋል።
የሴፍቲኔትና ሌሎችም የልማት ፕሮግራሞች ተፈጻሚ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት በየደረጃው ያሉት አመራሮች ከህዝቡ ጋር ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው አመልክተዋል።በፕሮግራሙ ያልተካተቱንም በመጨመር ውጤታማ ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ አድርገን ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀሰ ይጠበቅብናል ብለዋል።
የአምስተኛው ዙር የሰፍትኔት ፕሮግራም ዕቅድ ሲዘጋጅ አሁን ያለውን የትግራይ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አለመሆኑን የገለጹት ደግሞ የማህበራዊ ረድኤት ትግራይ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ዳይሬክተር አቶ ደስታ ገብረሚካኤል ናቸው።ፕሮግራሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀ ቢሆንም በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተለየ መልኩ ለማስኬድ የደረሰውን ጉዳት የሚያስረዳ ጥናት መደረጉን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ያስሚን ወሃብረቢ አስረድተዋል።በሀገሪቱ ባለፉት 20 ዓመታት መንግስት ሲያካሂደው የቆየው የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን የሴፍቲኔት መረሃ ግብር የጎላ አስተዋጽኦ ማድረጉን በመድረኩ መገለጹን ኢዚአ ዘግቧል።
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው