መንግሥት ቢቢሲ እና ሮይተርስን ጨምሮ – ሰባት ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ትግራይ ክልል ገብተው እንዲዘግቡ ተፈቀደ

መንግሥት ቢቢሲ እና ሮይተርስን ጨምሮ ሰባት ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ትግራይ ክልል ገብተው ስላለው ሁኔታ መዘገብ እንዲችሉ ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ።

በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ በተለያዩ አካላት የሚሰራጩ መሠረተ-ቢስ እና እና በፖለቲካ ሴራ የተሞሉ ሐሰተኛ መረጃዎች በእጁ እንዳሳሰበውም መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ለትግራይ ሕዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የሚቀርበው ጥሪ የመንግሥትን ሉዓላዊ ሥልጣን እና ኃላፊነትን ከማንኳሰስ ከሚደረጉ የፖለቲካ ፍላጎቶች እና ወገንተኝነት የፀዱ ሊሆኑ እንደሚገባም መንግሥት አሳስቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ በክልሉ ከሚገኙ 36 ወረዳዎች ውስጥ በ34 ወረዳዎች ሰብአዊ ድጋፍ መቅረቡን ጠቅሶ፥ በዚህም እስካሁን 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያለው፡፡

ከቀረበው ሰብአዊ ድጋፍ ውስጥ 70 በመቶው ድጋፍ በመንግስት ሲሸፈን 30 በመቶውን ደግሞ ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች መሸፈናቸው ነው የተገለጸው፡፡


Leave a Reply