ETHIO12.COM

ዛቻና ጫናው ቢበዛም መንግስት ከህዳሴ ግድብ ከሚመነጨው ኤሌክትሪክ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርን ዝርጋት እያጣደፈ ነው

May be an image of outdoors

የህዳሴ- ደዴሳ ባለ500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርን የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ቶማስ መለሰ ገለጹ፡፡

በተለያየ ምክንያት የተሰበሩትን ኢንሱሌተሮችን በአዲስ የመተካት ስራም ተጀመረል። እንደ ዳይሬክተሩ ገላጻ ኢንሱሌተሮቹን የመተካት ሥራው የተጀመረው በቅርቡ የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መስመሩን ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡

ኢንሱሌተር የመቀየር ሥራው ከህዳሴ- ደዴሳ – ሆለታ ድረስ ከተዘረጋው መስመር መካከል እስከ ደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ ባለው በሁለቱም የማስተላለፊያ መስመሮች በተተከሉ ምሶሶዎች ላይ እንደሚከናወን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በመስመሩ ላይ በተካሄደለት የፍተሻ ስራ መሠረት ከአንድ ሺህ 535 ምሶሶዎች በ312 ምሶሶዎች ላይ የሚገኙ ኢንሱሌተሮችን በሌላ የመቀየር ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።በቀጣይ ከደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ሆለታ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው ባለ500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በተመሳሳይ የመቀየር ሥራ እንደሚከናወን ተጠቁማል።

የደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ስምንት ባለ33 እና ሁለት ባለ132 እንዲሁም አንድ ባለ500 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን በአሁኑ ሠዓት ሁለት ባለ33 እና አንድ ባለ132 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ለነቀምቴ ከተማ እና አካባቢው ኃይል በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል፡፡

የህዳሴ ደዴሳ ሆለታ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ቻይና ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጅ በተሰኘ ኩባንያ መገንባቱ ይታወሳል ሲል ኢፕድ ነው የዘገበው።


Exit mobile version