Site icon ETHIO12.COM

ሙስጣፌ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ታጩ፤ ቅሬታ የገባቸው አሉ

አቶ ደመቀ መኮንን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃላፊነታቸው በተጨማሪ ደርበው እየሰሩ ላሉበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጣፌ መታጨታቸው ተሰማ። ክልሉና በውጭ አገር ያሉ የክልሉ ተወላጆች በዜናው ደስተኛ አይደሉም።

የአብዲሌ ወንበር ላይ ከተቀመጡ ጀምሮ እጅግ በሚገርም ሁኔታ በመላው አገሪቱ ተቀባይነት ያገኙት ሙስጣፌ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት የታጩት ገዢው ፓርቲ ብልጽግና በምርጫው ካሸነፈ አዲስ በሚዋቀረው ካቢኔ የሚካተቱ እንዲሆን ታስቦ ነው።

በሚመሩት ክልል ሁሉም ብሄረሰቦች እኩል ሆነው የሚስተናገዱበትን፣ ቋንቋውን ከቻሉ በሃላፊነት የሚመደቡበትንና ልዩነት የሌለበትን አሰራር በማስፈን ሰላም ያወረዱት ሙስጣፌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሆን መታጨታቸውን አስመልክቶ የክልሉን ተወላጅ ዲያስፖራ አባላትን አናገረን ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

የሜኖሶታ ነዋሪ የሆኑ የሶማሌ ተወላጅ ” ዜናውን ሰምተናል፤ ደስተኛ አይደለንም” ብለዋል። በሙስጣፌ ሹመት ሳይሆን ክልሉ ላይ የጀመሩትን ተግባር እንዲያጠናክሩ ከመመኘት አንጻር ባሉበት እንዲቀጥሉ ምኞታቸው እንደሆነም አስታውቀዋል። ክልሉ አካባቢም ተመሳሳይ እምነት እንዳለ ለማወቅ ችለናል።

በሌላ ዜና የሜኖሶታ ነዋሪ የሶማሌ ተወላጆች አሁን አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ የያዝቸውን አቋም እንዲላዘብ እየሰሩ መሆናቸው ታውቋል። ሰፊ የሶማሌና የኦሮሞ ማህበረሰብ ባለበት ሚኖሶታ የሶማሌ ድምጽና ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ በአካባቢው ያሉትን ሴናተር ማሳመናቸውም ታውቋል። ትናት ወደ ሜኖሶታ ያቀናው የክልሉ ሉዑል ቡድን ከባለስልታኑ ጋር እንዲገናኝ መመቻቸቱንም ጠቁመውናል።

ሙስጣፊ በትህነግና በትህነግ ደጋፊዎች ዘንድ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቀጥለው የሚጠሉ፣ በመላው አገሪቱ ደግሞ ተቀባይነትን ያገኙ የለውጡ ቱርፋት የሆኑ አዲስ መሪ መሆናቸው ይታወቃል።


Exit mobile version