ETHIO12.COM

የትግራይ ተወላጆች በወዳጅነት አደባባይ መከሩ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች በወዳጅነት አደባባይ በመገኘት የብልፅግና ፓርቲን ወክለው ለህዝብ ተወካዮች እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ከሚወዳደሩ እጩ ተወዳዳሪዎች ጋር ትውውቅ ማድረጋቸው ተገለጸ።

በመርሐግብሩ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሀፍታይ ገብረ እግዚአብሄርን እና በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጅ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎችና አባላት ተገኝተዋል ።

1 / 8

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከ ዳር በማቀፍ በጋራ ሀገር የሚያስቀጥል ፓርቲ ነው ብለዋል ።

የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን በመገንባት እና ዛሬ ላይ በማድረስ ትልቅ ሚና እንደነበረው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።ከለውጡ በፊት በተለያየ መንገድ በተፈጠሩ ክፍተቶች የትግራይ ህዝብ በብዙ መልኩ ተጎጂ ነበር ያሉት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሁንም የትግራይ ህዝብ ዳር ተመልካች እንዲሆን የሚሹ ሃይሎች አሉ፤ ያለንበት ምዕራፍ ግን እውነት ከሀሰት እየተለየ የሚወጣበት ወቅት ነው ብለዋል።ለሁሉም ነገር ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ሰላምን የሚያደፈርስን ማንኛውም እንቅስቃሴ በጋራ መመከት እንደሚገባም ጠቁመዋል ሲል የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ዘግቧል።



Exit mobile version