Site icon ETHIO12.COM

አዲስ አበባ-ፍቅረኛዬን አማገገጠ ያለ ወጣት ወርቃማ ጊዜውን በውህኒ ተባለ

በቂም በቀል ተነሳስቶ ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ የወጣትነት ጊዜውን በእስር እንዲያሳልፍ ተፈርዶበታል፡ የ25 ዓመቱ ተከሳሽ ዲሮ መንግስቱ ከበደ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539(1)(ሀ) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በፈፀመው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከሶ በእስራት ተቀጥቷል፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ሰውን ለመግደል አስቦ ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከለሊቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ክልል ልዩ ቦታው ሳሎ ጎራ መቃብር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሟች አሰፋው ከተማ የተባለውን ግለሰብ ከፍቅረኛዬ ጋር ወሲብ ፈጽሟል በሚል ምክንያት በቂም በቀል ተነሳስቶ ለጊዜው ካልተያዘው የወንጀል ተሳታፊ ዳንኤል ባይሳ /ባዩ/ ከተባለው ግለሰብ ጋር በመሆን ሟችን መጠጥ እንዲጠጣና እንዲሰክር ካደረጉት በኋላ ንፋስ እንቀበል ብለው ከመጠጥ ቤት አስወጥተው ከላይ በተጠቀሰው ስፍራ ሲደርሱ ያልተያዘው ግበረአበሩ ሟችን በመደብደብ መሬት ላይ ሲጥለው ተከሳሽ በድንጋይ ጭንቅላቱን በመምታት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጎታል፡፡

በመሆኑም በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ተከሳሽ በፈጸመው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ አድርጎታል፡፡በተጨማሪም ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው፣ የሰነድ እና ሌሎች ገላጭ ማስረጃዎችን አቅርቦ በማሰማቱና በማስመልከቱ እንዲሁም ተከሳሹ የተከሰሰበት ክስ በችሎት የተነበበለት እንዲከላከል የተጠየቀ ቢሆንም ወንጀሉን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ነህ ብሎታል፡፡

በመሆኑም ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሽ የቀደሞ ባህሪ እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ በመያዝ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ አቃቤ ህግ ፌስቡክ ገጽ

Exit mobile version