Site icon ETHIO12.COM

ለመምህራን በኪራይ ተላልፎላቸው የነበረውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲተላለፍላቸው ተወሰነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ሁለት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ2009 ዓ.ም ለመምህራን በኪራይ ተላልፎላቸው የነበረውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ቀደም ሲል የነበረው ካቢኔ በወሰነው መሰረት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፍላቸው ወሰኗል።

በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ለተለያዩ ተቋማት የተላለፉ የ40/60 እና 20/80 ቤቶችም የከተማ አስተዳደሩ ካለበት ከፍተኛ የወለድ ጫና ለማዳን ተቋማቱ ሙሉ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ እንዲተላለፉ ውሳኔ ማሳለፉን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። via ENA

Exit mobile version