የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ሁለት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል
በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ2009 ዓ.ም ለመምህራን በኪራይ ተላልፎላቸው የነበረውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ቀደም ሲል የነበረው ካቢኔ በወሰነው መሰረት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፍላቸው ወሰኗል።
በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ለተለያዩ ተቋማት የተላለፉ የ40/60 እና 20/80 ቤቶችም የከተማ አስተዳደሩ ካለበት ከፍተኛ የወለድ ጫና ለማዳን ተቋማቱ ሙሉ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ እንዲተላለፉ ውሳኔ ማሳለፉን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። via ENA