Site icon ETHIO12.COM

“ትግሬ ከሁሉም በላይ የላቀ ዘር እንደሆነ በይፋ እውቅናና ሥልጣን ይገባዋል”ትህነግ

ራሱን ለግማሽ ምዕተ ዓመት በተገንጣይ ስም ሰይሞ የሚንቀሳቀሰው ትህነግ በፓርላማ ከሰላሳ አምስት እስከ አርባ መቀመጫ እንደሚገባው ለማሳመን በቀጠራቸው የህዝብ ግንኙነት አጀንቶች አማካይነት እየሰራ መሆኑ ተሰማ። ትግሬዎች ከአገሪቱ የትኛውም ብሄር ይልቅ “የላቁና ቀደም ሲል ጀምሮ ገዢ” እንደነበሩ አድርገው ምክንያቶችን መከራከሪያና ማስመኛ ማቅረባቸውን ተመልክቷል።

“እኛ ልሂቃን ነን” ሲሉ ለሚከፍሏቸው የህዝብ ግንኙነት አጀንቶች የ”ማሳመኛ ነው” ያሉትን መረጃ እንዳስታጠቋቸው ታውቋል። ” ትግሬ ከጥንት ጀምሮ ገዢ፣ ነገስታትና በአገሪቱ ካሉ ዘሮች ሁሉ ከፍ ያለ ነው” ማለታቸውን ያስታወቁት በዚሁ በግዢው የህዝብ ግኝኙነቱ መስመር በቂ ግኝኙነት ያላቸው ኢትዮጵያዊ ናቸው።

በስቴት ዲፓርትመንትና በዋይት ሃውስ ዙሪያ ያለውን የህዝብ ግንኙነት ስራ የሚሰሩት ሁለቱ የሚታወቁ የህዝብ ግንኙነት ኤጀንሲዎች፣ ከትህነግ የወሰዱትን መረጃ አጠናክረው መንግስት በመስከረም ከመመስረቱ በፊት የድርድር ጫና ለመፍጠር እየሰሩ እንደሆነ ዜናውን ” ሕዝብ ይወቀው” ሲሉ መረጃውን ያካፈሉን ተናግረዋል።

የተናጠል የተኩስ አቁሙን ተከትሎ የመንግስት ሃይል ትግራይን ለቆ ሲወጣ ከጫካ ወጥቶ ወደ መቀለ የተመለሰው ትህነግ አሁን ህጻናትንና አረጋዊያንን ጾታ ሳይለይ እያሰለፈ የጥድፊያ ጦርነትና የፕሮፓጋንዳ ርብርብ የሚያደረገው ለዚሁ ድርድር የሚሰሩት ጫና ፈጣሪዎቹ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው ታስቦ እንደሆነም አመልክተዋል። ከዚሁም ጎን ለጎን የሚከፍልያቸው ታላላቅ ሚዲያዎች ይህንኑ በሚረዳ መልኩ እየሰበኩላቸው መሆኑንን አመላክተዋል። እነዚሁ ክፍሎች ይህንኑ “ስብከት” ይዘው በተሰማሩበት ከባቢያቸው እየቀሰቀሱ መሆኑን እንዳረጋገጡላቸው አመልክተዋል።

“ከትህነግ የሕዝብ ግንኙነት ተቀጣሪ ነጮች ጋር በስራ አግባብ ስንጫወት የነገሩኝ ሁሉ ያስገርማል” ያሉት የመረጃው ባለቤት ” ትግሬዎች ከሁሉም ዘር እኩል መታየት የለባቸውም፣ በቁጥር ቢያንሱም ኢትዮጵያን ያቀኑ ልዩ ዘሮች ናቸው። በመንግስት ከፍተኛ ውክልና ማግኘት አለባቸው” ሲሉ እንደነገሯቸውና ” አሁን ላይ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚባለውም ይኸው ነው” ብለዋል።

ትህነግ ወደ መቀለ ከማፈግፈጉ በፊት አውራምባ ታይም በሚባለው አፍቃሪ ትህነግ ሚዲያ ላይ ዳዊት ከበደ ስብሃት ነጋን ” እኛ በአገረ መንግስት ግንባታው ካለን ሰፊ ሚና አንጻር እንደ ሌሎች እኩል የስልጣን ድርሻ እንዴት ሊኖረን ይችላል” ሲል መጠይቁና ” አብይ እሺ ይልሃል? ማን እሺ ይልሃል” ሲሉ የንዴት መልስ መመለሳቸውን የዜናው ባለቤት አስታውሰው “አሳቡ አዲስ አለመሆኑንን በውቅቱ ስብሃት እየተወራጩ የመለሱት መልስ ያስረዳል” ብለዋል።

በቅርቡ ይህ ከመሰማቱ በፊት ” ሁልጊዜ ከትህነግ ጋር ከምንዋጋ ትግራይ ብትገነጠል ይሻላል” ሲሉ በፌስ ቡክ አሳባቸውን ለገለጹ ” በቁጥር ሳይሆን ኢትዮጵያን በመስራት ትልቅ አስተዋጽዖ የነበረውን ፣ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ልሂቃን የበዙበት የትግራይ ህዝብ ዝም ተብሎ አይገፋም” የሚል ምላሽ ሲሰጥ ነበር።

“ሁሉም ዘር ቢደመር እንኳት ትግሬን አይሆንም” ሲሉ ከነጮቹ ተከፋዮች መካከል ማብራሪያ የሰጣቸው እንዳለ ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ እስከ 40 በመቶ ፓርላማ ውስጥ ውክልና በማግኘት ቀሪውን አስራ አንድ በመቶ በማግባባትና በመደለል ወደ ራሳቸው አድረገው መንግስት ለመመስረትም ሃሳብ እንዳላቸው አመለክተዋል።

ትህነግ ለዲሞክራቶች፣ ለሪፐብሊካኖች፣ ለሃይማኖቶች ጥምረት፣ለጥቁር አፍሪካ አሜሪካኖች ጥምረት፣ ለዋይት ሃውስ፣ ለኮንግረንስ፣ Lesbian, Gay, Bisexual and Transgender. q ለሚባሉት ጥምረቶችና ለተቀረው የህብረተሰብ ክፍል በህዝብ ግንኙነት የሚሰሩ ስምንት ታዋቂ ኤጀንቶች እንዳሉት መዘገባችን ይታወሳ። በዚህ ዘገባ የተጠቀሰውን ዝርዝር ጉዳይ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ።

የአዲስ አበባ የኢትዮ12 ተባባሪ ይህንኑ የትህነግ አሳብና እቅድ አስመልክቶ ያነጋገራቸው የብልጽግና ሰዎች ” ድሮም እኔ ልዩ ነኝ፤ እንዳሻኝ ልሁን፣ ከሶማሌ፣ ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከጋምቤላ፣ ከኦሮሚያና አማራ እኩል እንዴት እሆናለሁ” ብሎ ወደ ትግራይ ማፈግፈጉን ገልጸዋል። እዛም ሆኖ መንግስት ለመመስረት እነማንን ያሰባስብ እንደነበር ማስታወሱ በቂ እንደሆነ አመልክተዋል።

ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ” ችጋር እየገረፈህ መመጻደቅ፣ በችጋር መነገድና ችጋርን መሳሪያ አድርጎ መቆመር መለኪያ ከሆን፣ ሴራና ግፍ ማሳያ ከሆኑ በትክክልም የላቁ ናቸው” ብለዋል። እኚሁ አስተያየት ሰጪ ይህን አስመክቶ ሰፊ ዝግጅት እንደሚያዘጋጁም ገልጸዋል።

ትህነግ ኦሮሞን “ጠባብ”፣ አማራን “ትምክህተኛ”፣ ሊሎችን “አናሳ” እያለ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት መግዛቱን በማስታወስ የሶማሌ ክልል መሪ አቶ ሚስጣፊ ” የሶማሌ ሕዝብ በቁጥር ከትግራይ ሕዝብ ይበልጣል ነገር ግን የፓርላማ ውክልናችን ከትጋራይ በታች ነው። ይህ አገባብ አይደለም ” በማለታቸው ” ከትግሬ እኩል ሊሆን አማረው” በሚል ከሌሎች የክልል አመራሮች በተለየ የትህነግ የትችት ዒላማ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

በመንግስት በኩል ውክልና በሕዝብ ቁጥር እንደሚሆን፣ እዛ ላይ ምን መለሳለስ እንደሌለ፣ የትግራይ ክልል ልክ እንደ ቤኒሻንጉል ወይም ጋምቤላ ወይም ሲዳማ ወይም አፋር ወይም … እኩል ተደርጎ እንደሚታይ መገለጹ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ” ነጥሎ መምታት” በሚል ስልት ከህዝብ ለመነጠል ሰፊ ዘመቻ እንደነበር ተባባሪያችን ያነጋገራቸው አስታውሰው፣ ዛሬም መንግስት ከዚ የተለየ አቋም እንደማያራምድ አመልክተዋል።

ሟቹ አቶ መለስ ” ታላቅ ነበርን ታላቅ እንሆናለን” በሚል መፈክር ይታወቁን እንደነበር። ኢትዮጵያን እየመሩ ” እንኳን ከእናንተ ተወለድኩ” በሚል ባደባባይ ዘራቸውን ሲያሞካሹም እንደነበር ይታወሳል።


Exit mobile version