የአሜሪካው ስፔስ ኤጀንሲ ናሳ እና ሀዋይ ዩኒቨርሲቲ በትብብር በሰሩት ጥናት እንዳመላከቱት ጨረቃ በራሷ ዛቢያ ላይ የምታደርገው ተፈጥሯዊ ዑደት መዛባትና የአየር ንብረት ለውጥ በፈረንጆቹ 2030 ሊከሰት ለሚችል የጎርፍ አደጋ ስጋት መንስኤ ሊሆን ይችላል ተባለ፡፡
አሜሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተሰራው በዚህ ጥናትም እንደተመላከተው÷ከፍተኛው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚከሰተው በፈረንጆቹ 2030 ሲሆን ክስተቱ ለ አስር ዓመታትም ሊቀጥል እንደሚችል ተተንብይዋል፡፡
የአሜሪካ የባህር እና የከባቢ አየር አስተዳደር እንዳስታወቀው በፈረንጆቹ 2019 በአሜሪካ 600 የሚደርስ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲከሰት ይህ አሃዝ ግን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ በብዙ እጥፍ ሊጨምር ይችላል ነው የተባለው፡፡
ፊል ቶምሰን የተባለው የሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና ዋና የጥናቱ መሪ እንዳመላከተው÷ በጨረቃ ዑደት መዛባት ምክንያት የሚከሰተው ይህ የጎርፍ አደጋ በሀሪኬን ምክንያት ከሚደርሰው ይልቅ በመጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡
እንደ ጥናቱ በአሜሪካ በወር ከ 10 እስከ 15 ያህል ጊዜ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ከተከሰተ ተፅዕኖው በንግድ ተቋማት እና በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች (ፓርኪንጎች) ላይ ስለሚበረታ በርካቶች ከስራቸው ሊስተጓጎሉ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡
የጎርፍ አደጋው ውሃማ በሆኑ የአሜሪካ ዳርቻዎች እንዲሁም እንደ ሃዋይ፣ ጉዋም፣ እና አላስካ ባሉ አካባቢዎች ሊበረታ እንደሚችልም ነው የተገለፀው፡፡
ኢ-መደበኛ የጨረቃ ዑደት አዲስ ክስተት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 1728 ተከስቶ እንደነበረም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
ምንጭ÷አልጀዚራ
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት