በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል።
የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አሕመድ በጎርፉ የተጎዱት ከ600,000 በላይ ሰዎች እንደሚሆኑና ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል።
” ምግብም፣ መድኃኒት የሚበቃ የላቸውም ችግሩ ከፍተኛ ነው። የተፈናቀሉት ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። …ትንሽ ከፍ የሚል ቦታ ከውሃ ትንሽ ወጣ ብለው ነው የተቀመጡት። ሰው በእግር ውሃው ውስጥ ሂዶ አህያም ያላቸው ለትራንስፖርት እየተጠቀሙ ከፍ ወዳለ ቦታ እየሄዱ ነው አሁን ከከተማው ብቻ ነው የወጡት እጂ ብዙም ከወንዙ አራቁም ” ነው ያሉት።
ሴቶችና ህፃናት በምን ሁኔታ ይገኛሉ ?
አቶ አብዲራዛቅ በሰጡን ማብራሪያ፥ “እደዚህ አይነት ችግር ሲመጣ መጀመሪያ የሚጎዱት ሴቶችና ልጆች ናቸው። እስካሁን የሞቱት ጠቅላላ 28 ሰዎች ሲሆኑ ከ28ቱ ወደ ስምንት የሚሆኑት ሴቶች ናቸው” ብለዋል።
ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ምን ይመስላል ?
ዳይሬክተሩ ይህንን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፥ ” ያለነውን ሪሶርስ ተጠቅመን ከመንግሥትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሆነን የምንችለውን ድጋፍ እያረግን ነው። ግን ችግሩ በጣም ትልቅ ስለሆነ ለሁሉም ሰው መድረስ የሚያስችለን ሪሶርስ የለም። ከሁሉም አቅጣጫ የተሰበሰበ ገንዘብም ራሱ እስካሁን ሊበቃ አልቻለም ” ብለዋል።
ለተፈናቀሉት ሰዎች ጥሬ ገንዘብ እየሰጠን ነው ያሉት አቶ አብዱራዛቅ፥ እደፍላጎታቸው እዲጠቀሙ 300 ሺሕ ለሚሆኑ አባውራዎች ለእያንዳንዳቸው 7 ሺሕ 700 ብር፣ ለ1 ሺሕ 200 አባውራዎች የእቃ ድጋፍ እንዳደረጉ ጠቅሰዋል። አሁን ላይ በጣም የሚያስፈልጋቸው ምግብ እንዲሁም የሚያድሩበት ቤት እንደሆነም ጠቁመዋል።
የጎርፍ አደጋው እየጨመረነው ወይስ እየቀነሰ ?
ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው ዳይሬክተሩ፣ “#የመቀነስ ነገር የለም፣ ዝናቡ እየዘነበ ነው በጣም የወንዙ ውሃ ከፍተኛ እየሆነ ነው። አሁን #ስጋቱ እዳለ ነው የሚቀንስም አይመስልም። ዝናቡም የወንዙ ውኃም አንድ ላይ ተጨምሮ ችግር እየሆነ ነው መንገዶች ሁሉም ተዘጋግተዋል” ሲሉ አስረድተዋል።
ድጋፉን ለማድረስ በጣም ፈተና የሆነው ጉዳይ ምንድን ነው ?
” ፈታኝ የሆነው ነገር መቀሳቀስ አልቻልንም። ሁሉም ቦታ ውሃ ነው። ልጆቹ [ድጋፍ ሰጪዎቹ] በብዛት በጋሪ ነው የሚንቀሳቀሱት። ሕዝቡም እደዛ ነው የሚንቀሳቀሰው። ሰው የሚበላ አዞም ይኖራል፤ይፈራሉ። በመኪና መሄድ አይቻልም። ውኃው በጣም እየጨመረ ነው። በጣም አስቸጋሪ ነው አይደርስም ያልንበት ቦታ ጎርፉ እየደረሰ ነው ” ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል።
አክለውም፥ ” ብዙ ሰውም በዚህ ምክንያት እየተፈናቀለ ነው። እደዚህ አይነት ጎርፍ አይተን አናውቅም። ህዝቡ ራሱ እደዚህ አይነት ጎርፍ አላየንም የሚል ነገር ነው ያለው። በሜትሮሎጅ መረጃ መሠረት ጎርፍ እንደሚኖር ለህዝቡ መነገር ነበረበት። በሚያስፈልገው ልክ አልተሰራም መሰለኝ። ለወደፊትም ከተማው በወንዙ በኩል ሳይሆን በሌላኛዉ በከፍታው በኩል ቢያድግ ጥሩ ነው” ሲሉ አቶ አብዲራዛቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
በመጨረሻም፣ መንግሥትና ከሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም፣ ጉዳቱ በጣም ከባድ ስለሆነ ድጋፍ ተፈናቃዮችን መዳረስ እንዳልቻለ፣ ርብርብ በማድረግ ሕዝቡን መታደግ እንደሚገባም ጥሪ ቀርባል።
ከ tikvahethiopia የተወሰደ
- ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አርተፊሻል ቦይ በመስራት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆን ትችላለች፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሊፈጠር የቻለው፤ የኢትዮጵያ የአፋር ቦታ ከባህር ወለል በታች እስከ 110 … Read moreContinue Reading
- ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፤ ተጠናክሮ ክምሩ እንደሚሰራበትና ግሽበትን በዓመቱ መጨረሻ 20 ከመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተሰማ። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና የማበረታቻ መደረጉ ለውጥ ቢያሳይም በቂ እንዳልሆነ ተመለከተ። … Read moreContinue Reading
- የኮሚሽኑ የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነየአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ … Read moreContinue Reading
- መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው። የግምገማው ተሳታፊዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ጨምሮ በርካታ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወኑን አድንቀው፤ ሆኖም” ድጎማው … Read moreContinue Reading
- በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነውበቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል። ምርቱ በተባለው ወር ሲጀምር የሲሚንቶ ዋጋ አሁን ካለበት በግማሽ እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከመጋቢት በሁዋላ ፋብሪካው በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን ያስወግዳል። ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ … Read moreContinue Reading