የአሜሪካው ስፔስ ኤጀንሲ ናሳ እና ሀዋይ ዩኒቨርሲቲ በትብብር በሰሩት ጥናት እንዳመላከቱት ጨረቃ በራሷ ዛቢያ ላይ የምታደርገው ተፈጥሯዊ ዑደት መዛባትና የአየር ንብረት ለውጥ በፈረንጆቹ 2030 ሊከሰት ለሚችል የጎርፍ አደጋ ስጋት መንስኤ ሊሆን ይችላል ተባለ፡፡
አሜሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተሰራው በዚህ ጥናትም እንደተመላከተው÷ከፍተኛው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚከሰተው በፈረንጆቹ 2030 ሲሆን ክስተቱ ለ አስር ዓመታትም ሊቀጥል እንደሚችል ተተንብይዋል፡፡
የአሜሪካ የባህር እና የከባቢ አየር አስተዳደር እንዳስታወቀው በፈረንጆቹ 2019 በአሜሪካ 600 የሚደርስ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲከሰት ይህ አሃዝ ግን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ በብዙ እጥፍ ሊጨምር ይችላል ነው የተባለው፡፡
ፊል ቶምሰን የተባለው የሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና ዋና የጥናቱ መሪ እንዳመላከተው÷ በጨረቃ ዑደት መዛባት ምክንያት የሚከሰተው ይህ የጎርፍ አደጋ በሀሪኬን ምክንያት ከሚደርሰው ይልቅ በመጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡
እንደ ጥናቱ በአሜሪካ በወር ከ 10 እስከ 15 ያህል ጊዜ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ከተከሰተ ተፅዕኖው በንግድ ተቋማት እና በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች (ፓርኪንጎች) ላይ ስለሚበረታ በርካቶች ከስራቸው ሊስተጓጎሉ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡
የጎርፍ አደጋው ውሃማ በሆኑ የአሜሪካ ዳርቻዎች እንዲሁም እንደ ሃዋይ፣ ጉዋም፣ እና አላስካ ባሉ አካባቢዎች ሊበረታ እንደሚችልም ነው የተገለፀው፡፡
ኢ-መደበኛ የጨረቃ ዑደት አዲስ ክስተት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 1728 ተከስቶ እንደነበረም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
ምንጭ÷አልጀዚራ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን