Site icon ETHIO12.COM

በጀት ዓመት ሀሰተኛ ደረሰኝ ሲታተምባቸው የነበሩ 31 ህገ-ወጥ የካሽ ሬጂስተር ማሽኖች ተይዘዋል

በሀሰተኛ ማንነት የሀገርንና የህዝብን ሀብት ለመዝረፍ ሲውሉ የነበሩ 31 የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎቹ የተያዙት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ደረሰኝ ግብይት መደረጉን የሚያረጋግጥና ለታክስ አሰባሰብ አገልግሎት የሚውል በመሆኑ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ልውውጥ ሳይኖር ደረሰኝ መቁረጥ እና ማሰራጨት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 መሰረት የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቅሷል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በያዛቸው ሕገ-ወጥ ማሽኞች ብቻ ግብይት ሳይኖር የ3.2 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው ግብይት እንደተፈፀመ ተደርጎ ደረሰኝ በመቁረጥ ለታክስ ስወራ እና ማጭበርበር ውሏል ብሏል፡፡

በእነዚህ ማሽኖች ታትመው የተሰራጩ ሀሰተኛ ደረሰኞች በአንዳንድ ግብር ከፋዮች ግብርን አሳንሶ ለማሳወቅ ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡

ሀሰተኛ ደረሰኝ አሳትሞ በማሰራጨት ወንጀል ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ 26 ሰዎችም ተይዘው ጉዳያቸው በሕግ በመታየት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡

በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ በግብይት ወቅት ደረሰኝ ያልቆረጡ 401 ደርጅቶች በክትትል ተለይተው የ20,450,000 ብር አስተዳደራዊ ቅጣት የተወሰነባቸው ሲሆን በድርጊቱ ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ 532 ሰዎችም በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው በወንጀል እንዲጠየቁ መደረጉን ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡ OBN

Exit mobile version