ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ አዘጋጅቶ ለተለያዩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በመሸጥ በከፍተኛ የማጭበረበር ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በፊንፊኔ ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው አድራሻው የማይታወቅ ሰለሞን ሙሉ ከውን በተባለ ግለሰብ ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት በዚሁ መታወቂያ የንግድ ፍቃድ በማውጣት የማሽነሪዎችና የመሣሪያዎች ኪራይና ሽያጭ የንግድ ዘርፍ ላይ ተመዝግቦ ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ ሳያደርግና የሸጠው እቃ ሳይኖር ሐሰተኛ የሽያጭ ደረሰኝ ለተለያዩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች በ30 ቢሊዮን 152 ሚሊዮን 434 ሺህ 002 ብር ከ03 ሣንቲም በመሸጥ መሆኑ ታውቋል።
ግለሰቡ የማጭበርበር ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ለበርካታ ጊዜያት ተደብቆ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፊንፊኔ ከተማ ገቢዎች ጋር በመተባበር ባደረገው ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን አስታውቋል ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ኅብረተሰቡም ወደ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ በአካል ቀርቦ ተጨማሪ መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጥሪ ማቅረቡን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ዜናው የፌደራል ፖሊስ ነው
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል