Site icon ETHIO12.COM

ሶስት የውጭ ድርጅቶች ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በመንቀሳቀሳቸው የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለሶስት ወራት ታገዱ

fact check

ሶስት የውጭ ድርጅቶች ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በመንቀሳቀሳቸው የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለሶስት ወራት ታገዱ ሲል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አሳውቋል፡፡

አንደኛ MSF HOLLAND ሁለተኛ NORWEGIAN REFUGEE COUNCIL እና ሶስተኛ AL MAKTOUME FOUNDETION የተባሉ የውጭ ድርጅቶች የኢትዬጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ በሰጣቸው ፍቃድ በህጋዊነት በተለያዩ የሰብዓዊ ስራዎች ተሰማርተው እየሰሩ የቆዩ ድርጅቶች ሲሆኑ የድርጅቶቹን እንቅስቃሴ በተመለከተ ፍቃድ ሰጪው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በሚያደርገው ክትትል መሰረት ድርጅቶቹ ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በመንቀሳቀስ፤

ድርጅቶቹ ከተቋቋሙት አላማ ውጭና የሃገርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው እንዲታረሙ በተደጋጋሚ ከድርጅቶቹ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ቢደረግም ሊያስተካክሉ ስላልቻሉ አጠቃላይ ምርመራ ተደርጎ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 77(4) መሰረት አጠቃላይ የድርጅቶቹ እንቅስቃሴ ለሶስት ወራት የታገዱ መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አሳውቋል፡፡

Exit mobile version