Site icon ETHIO12.COM

ዶ/ር ኮንቴ ” እውነቱን እናውቀዋለን፣ ትህነግ ጨፍጭፎናል” በአፋር የሶስት ቀን ሃዘን ታወጀ፤ ትህነግ ተጨማሪ 8 የቤተሰብ አባላት ገደለ

“አፋርን መውረርና የአፋርን ህዝብ መጨፍጨፍ ጠንካራ ያደርገናል። በሌላ በኩል ደግሞ በአፋርና በትግራይ ክልል ሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ይገለዋል። ቅጥፈታችሁ እየወየበና እየደበዘዘ፣ እውነት ወደ አደባባይ እየመጣች ነው። እውነቱን እናውቀዋለን። ተጠያቂዎቹ እናንተ ናቹህ” ሲሉ አምርረው ያስታወቁት ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ናቸው።

ዶክተር ኮንቴ ይህን ያሉት ጌታቸው ረዳ ” ከደሙ ንጹህ ነን” በሚል ጭፍጨፋውን አሸባሪው ትህነግ ሳይሆን መንግስት እንድፈጸመው ጥቅሰው በቲወተር ገጹ ላሰራጨው ሲመልሱ ነው።

ዶ/ር ኮንቴ ጭፍጨፋው ሲፈጸም ጋሊኮማ ላይ የትህነግ ሃይል ማሳከር ሲፈጽም በስፍራው የመንግስት ሰራዊት እንዳልነበር አስታውቀዋል። በትናንትናው ዕለት ስምንት የቤተሰብ አባላት በሚዘገንን ሁኔታ መጨፍጨፋቸውን ይፋ ባደረጉበት የቲውተር አውዳቸው ላይ እንዳስታወቁት የዩኒሴፍን ተዓማኝነት ሁሉ ጥርጣሬ ውስጥ እንደሚያስገቡ አመላክተዋል።

የተደረገውን ተኩስ አቁም ተከትሎ ለምን ጉዳይ አፋርን እንደወረረና፣ በምን ምክንያት 240 ንጹሃንን ከተጠለሉበት ድረስ ዘልቆ ለመጨፍጨፍ እንደወሰነ ትህነግ እስካሁን በገሃድ በዝርዝር ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ ዶክተር ኮንቴ እንዳሉት በስፍራው ያልነበረውን የመከላከያ ሃይል አውግዞ አጭር የቲውተር ሃሳብ ለጥፏል።

አንድ መቶ ሰባት ህጻናት የተጨፈጨፉበት ትዕንት ቆስለው ህክምና በማድረግ ላይ ብሚገኙ አካላት ምስክርነት እየተሰጠበት ቢሆንም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠበትም።

ትግራይን ሄዶ የማየት እድል ያልነበረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከማንና እንዴት እንደሚያገኘው ግልጽ ሳይሆን ተከታታይ መረጃ ሲያከታትል እንዳልነበረ፣ ዛሬ በአፋር ሆስፒታል ያሉ እማኞችን ሄዶ ለማነጋገር ይህን ያህል ጊዜ መውሰዱ የዶክተር ዳንዔልን አቋም ይበልጥ ጥያቄ ውስጥ አስገብቷል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ትህነግ ጭፍሮቹን አሰማርቶ አስገድዶ መድፈር ፈጽሟል። ሕጻናትን ጭፍጭፏል። ዝርፊያ አካሂዷል። ከፍተኛ የተባለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል።

ዛሬ ረፋዱ ላይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ወደ ስፍራው ቡድን መላኩን አውስቶ፣ ስጋት እንደገባው ጠቁሞ አጭር ጥሪ አሰምቷል። ድርጅቱ ትህነግ በወረራቸው አካባቢዎች ስለተፈናቀሉ፣ ስለተገደሉና ስለተዘረፉ ሰዎች እስካሁን ያለው ነገር የለም። ከንግሊዝ ተመልሰው ድርጅቱን የሚመሩት ዶ/ር ዳንኤል የማይካድራውን ጭፍጨፋ ሪፖርት ከዳፈኑ በሁዋላ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ተዓማኝነታቸው እየወረደ እንደሚገኝ በርካቶች እያወሱ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ክልል መንግስት በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች የሶስት ቀን ሃዘን አውጇል። ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጓል።

ዶክተር ኮንቴ የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራር፣ ኢትዮጵያዊ አቋማቸው ላይ መዛነፍ የሌላቸው፣ ህዝብ የሚወዳቸው ፖለቲከኛ ናቸው።

በአፋር ንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ በተፈጸመ ማግስት መንግስት የዜጎቹን ሰላም ለማስጠበቅ ሲል በይፋ የማጥቃት እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ እንደሚሰጥ አስቀድመው የገለጹ የአሜሪካ ባለስልጣናት ነበሩ።


Exit mobile version