Site icon ETHIO12.COM

የመስከረም የምግብ ዋጋ ንረት በ10 ዓመታት ከተመዘገበው ትልቁ ሆነ

FAO – የተባበሩት መንግስታት የምግብ እርዳታ ድርጅት እንዳስታወቀው እኤአ 2011 መስከረም የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጭማሬ ማሳየቱን አመለከተ። ጭማሪው በአስር ዓመት ውስጥ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።

ፋኦ 130 አማካኝ የዋጋ ዝርዝር ነጥቦችን ያየ ሲሆን 1 ነጥብ 2 ከመቶ ከነሃሴ ወር ጭማሬ አሳይቷል፤ የአቅርቦት እጥረት እና ለአብዛኛው የአለም ህዝብ ዋነኛ ምግብ የሆኑት የስንዴና የፓልም ዘይት ፍላጎት መጨመር ለዋጋ መናር መንስኤ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመስከረም ወር በንግድ መመዘኛ ሲታይ አምስት በዓለም ላይ ዋነኛ የምግብ ሸቀጦች እኤአ መስከረም 2020 ከነበሩበት የ32 ነጥብ 8 ከመቶ ጭማሬ አሳይተዋል፡፡


READ MORE


የጥራጥሬ ዋጋ በነሃሴ ወር ከነበረበት 2 ከመቶ ጭማሬ አሳይቷል፤ በአለም ላይ ከፍተኛ የሥንዴ ዋጋ ጭማሬ የታየ ሲሆን ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አኳያ ስንዴን ወደ ውጪ ገበያ ማውጣት አዳጋች ሆኗል፡፡

“ከዋነኛ ጥራጥሬዎች መሃክል ስንዴ የቀጣይ ሳምንታት ትኩረት ነው”ያሉት የፋኦ ኢኮኖሚስት አብዶልረዛ አባሲያን ፈጣን የዋጋ ጭማሬው ቅድሚያ ተሰጥቶት ይታያል ብለዋል ፡፡

የፓልም ዘይት በአለም አቀፍ ደረጃ ፍላጎት መጨመሩና የዚሁ አምራች የሆነችው ማሌዢያ በሰራተኛ እጥረት በሙሉ አቅሟ አለማምረቷም በ10 አመት ከፍተኛው ጭማሬ እንዲያሳይ አድርጓል ብሏል፡፡

የወተት ውጤቶች እንዲሁም ስኳር በመጥፎ የአየር ጸባይ የስኳር ላኪ በሆነችው ብራዚል መከሰት የዋጋ ጭማሪ እንዲያሳዩ ሆኗል፡፡ በአንፃሩ የስጋ ዋጋ ቀደም ካሉት ወራት በመስከረም ወርም ጭማሬ አላሳየም ሲል አናዶሉን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version