Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያን በፕሮፓጋንዳ ለማተራመስ እጅግ የተቀናጀ ዘመቻ ተጀምሯል

በኢትዮጵያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ጦርነት እየጦፈ የሚሄድበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነን። ዜጎችም በመንግስት ኃላፊነት ላይ ያሉም በደንብ ልብ ልንል የሚገባን ሁኔታ ከፊታችን እየመጣ ነው።

አሸባሪው ቡድን እና ጋላቢዎቹ በየሚዲያዎቻቸውና የዲጂታል ሰራዊት ቅጥረኞቻቸው የተቀናጀ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሊያጧጡፉ ተዘጋጅተዋል።

ይህ የመረጃ ውጊያ ልዩ ልዩ ዘዴ የሚከተል ቢሆንም አምስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ያነጣጠረ ነው፦

1ኛ- ዜጎች በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጡና ከመንግስት ጋር መተባበር እንዲለግሙ /እንዲያቆሙ ታሳቢ ያደረገ፤

2ኛ- የአሸባሪው ኃይሎች አዲስ አበባን ለመቆጣጠር “ይሄን ያህል ቀራቸው” በሚል በዜጎች ላይ መረበሽ እንዲፈጠርና መንግስት ውጣሬ ውስጥ እንዲወድቅ ያለመ፤

3ኛ- የመንግስት ኃላፊዎች ሀገር ጥለው እንዲሸሹ ከፍተኛ ቅስቀሳ ይኖራል (ጥገኝነት ለመስጠትም ግፊት ይኖራል -ከተሳካላቸው ይጠቀሙባቸዋል)

4ኛ- መከላከያ ውጊያ እንዲያቆምና ትጥቁን እንዲፈታ ከፍተኛ ጥሪ ይካሄዳል

5ኛ- በጥቅሉ ሁሉ ነገር እንዳለቀለትና እንዳበቃለት እጅግ የተቀናጀ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ለማካሄድ ጅምር አለ

ከዚች ሰዓት ጀምሮ ይህን እውነታ እውቀን ሁላችንም በቻልነው አቅም መግጠም አለብን! ትዊተር የሌላችሁ ክፈቱ – ከፍታችሁ የተዋችሁት በሚገባ ተጠቀሙበት።

በፈስቡክም ዜጎች በሽብር ቡድኑና በጋላቢዎቹ ወሬ እንዳይራበሽ በንቃት የስነልቦና መረጋጋት በሚፈጥሩ መረጃዎች አየሩን መያዝ ያስፈልጋል። offline ያሉ ዜጎችም በሚነዛው ወሬ እንዳይረበሹ በተቻለን አቅም ሁሉ የመረጃውን ውጊያ መጋፈጥ ግድ እለብን! ስለሰሜን ዕዝ ተቆጭተን እኔም ወታደር ነኝ ካልን ዘንዳ ቢያንስ
እጃችን ላይ ያለውን መሳሪያ (ስልካችንን) ተጠቅመን የመረጃውን ውጊያ በተባበረ ክንድ እንመክትን!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት

_ አካባቢህን ጠብቅ
_ ወደ ግንባር ዝመት
_ መከላከያን ደግፍ


Exit mobile version