Site icon ETHIO12.COM

ጅቡቲ ኢትዮጵያ ለማጥቃት መረማመጃ እንደማትሆን በይፋ አስታወቀች

“ጅቡቲ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ታወድሳለች። ምንም ይሁን ምን ግን ይህ አጋርነት በየትኛውም ሀገር ላይ ያነጣጠረ አይደለም” Djibouti appreciates its strategic partnership with the United States and for sure this partnership is not oriented against any country ሲሉ የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ።

ሚኒስትሩ ሞሃመድ አሊ የሱፍ ይህን ያሉት ቢቢሲ በጅቡቲ የአሜሪካ ጦር አዛዥን ጠቅሶ ያስተላለፈውን ዜና ተከትሎ ነው። ቢቢሲ ሁለት ጊዜ ዕርዕስ በመቅየር ያተመው ዜና በጅቡቲ ያለው የአሜሪካ ሃይል ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ የመውሰድ ዝንባሌ እንዳለው ዘግቦ ነበር።

ከሙያና ከስርዓት ባፈነገጠ መልኩ ቢቢሲ ባሰራጨው ዘገባ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላለው ቀውስ ወታደራዊ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አትሟል። በጅቡቲ የሚገኘውን የአገሪቷን የጦር መሪ ጀነራል ዊሊያምን ጠቅሶ ቢቢሲ ማስፈራሪያውን ከዘገበ ከሰዓታት በኋላ ዜናውን መልሶ አስተካክሎ “በትግራይ ያለው ቀውስ ለቀጣናው ስጋት ነው ስትል አሜሪካ ገለጸች” በሚል እንዲነበብ አድርጓል። ይህንኑ ውስጡ መርዛማ የሆነውንና ኢትዮጵያን ለማናጋት ዓላማ አድርጎ የተዘገበ ዜና አዲስ አበባ የተቀመጠው ቢቢሲ አማርኛ እንዳለ አውርዶ ዘግቦትም ነበር። ቢቢሲ አማርኛ በሚሊዮን የሚቆተር ሕዝብ መስቀል አደባባይ ወጥቶ ትህነግን እንደማይፈልግና የዓለም መገናናዎችን ሸውራራነት በአደባባይ ሲያወግዝ ” በስር ሺህ የሚቆጠሩ” ብሎ ወዲያው በማህበራዊ ገጹ ላይ ውግዘት ሲደርስበት “አብዛኞች” ብሎ ድጋሚ ዜና ለመስራት መገደዱ ይታወሳል።

የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ በቲውተር ገጻቸው አንዳንዶች የጅቡቲን ግዛት ለጎረቤት ሀገራት ጣልቃገብነት ጥቅም ላይሊውል ይችላል በሚል ስጋት እንዳደረባቸው አመልክተው፣ የጅቡቲ መንግስት ከጎረቤት አገራት ጋር ካለው ግንኙነት አንጻር ስጋት ሊኖር እንደማይገባ ጠቁመዋል።

ጄኔራል ዊሊያም ለቢቢሲ ቃለ ምልልስ ሲሰጡ በጅቡቲ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሽብርተኝነትን የመዋጋትና ዜጎቻቸውን የመጠበቅ ተልእኮውን እንዴት እየፈፀሙ እንደሆነ ማስረዳታቸውን ባለስልጣኑ በተከታታይ ቲውት አድርገዋል።

ከቃለ ምልልሱ ይዘት ውጪ ቢቢሲ ኢትዮጵያ ላይ ከያዘው የተጣመመ አቋምና ከሚከተለው ዓላማ አንጻር አሜሪካ ከጅቡቲ የጦር ማዘዣዋ ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ልታደርስ እንደምትችል ማስፈራሪያ የሳፉበትን ምክንያት የመንግስት ሚዲያዎች በይፋ አውግዘው ጽፈዋል።

“የቢቢሲ የቀደመው ዘገባ ምዕራባዊያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ በቀጣይ ሊስሩት ያሰበውን ጉዳይ በግልጽ ያሳየ ነው ያሉት መምህሩ፤ ምዕራባውያኑ በሌሎች አገራት ላይ የሚወስዱት እርምጃ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ቅቡልነት እንዲያገኝ የሕዝብ አስተያየት ቅርጽ የመስጠት ሥራን በሚዲያዎቻቸው ይሠራሉ” ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

ይህ ዘገባ ይፋ ከመሆኑ በፊት ሄርማንኮሆን ለትህነግ እህል በአየር የመጣል አማራጭን አሜሪካ ለታስብበት ይገባል ሲሉ አስታውቀው ነበር። አንድ ነባር ጀነራልም ስለ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ጽሁፍ አሰራጭተው ነበር።

አሜሪካ ብወታደራዊ ጣልቃ ግብነት በሄደችበት ሁሉ አገር አፍርሳና ዜጎችን መኖሪያ አልባ ከመውጣት፣ ዜጎቿን ከማስጨረስ ውጭ ምንም ዓይነት በጎ ታሪክ እንደሌላት ያመከነቻቸውንና ተዋርዳ የወጣችባቸውን አገር በመጥቀስ ሃሳቡን ያወገዙም ጥቂት አይደሉም።

የቢቢሲ ዘገባ ለትህነግ ደጋፊዎች እጅግ ደስታ የሰጠና በስፋት የተቀባበሉት ዜና ሆኖ ውሎ ነበር። በሌላ በኩል በአገር ቤት ሁሉም ዜጎች በሚባል ደረጃ በትህነግና በሽብር ተግባሩ ላይ ተመሳሳይ አቋም በመያዛቸው ዜናው የታሰበውን ያህል ድንጋጤ አልፈጠረም። አንዳንዶች እንደውም ” ይምጡና ይሞክሩ” በሚል በሶማሌ የአሜሪካ ወታደሮች ሲጎተቱ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ገጾቻቸው ሲያሰራጩ ነበር።

Exit mobile version