Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ላይ የሃሰት መረጃ ለመርጨት ታዋቂ ሚዲያዎች ሱዳን እየዶለቱ መሆኑ ታውቀ

ኢትዮጵያ ላይ ሆን ብለው ሀሰተኛ መረጃዎችን በመርጨት የሚታወቁት የምዕራባውያን ሚዲያዎች በሱዳን እየዶለቱ መሆናቸውን ተሰማ።

በኢትዮጵያ ላይ ለይተው ሀሰተኛ መረጃዎችን በማቀናበርና በመርጨት የሚታወቁት የምዕራባውያን የሚዲያ ተቋማት ተወካዮች በካርቱም በሚደረግላቸው ድጋፍ በሱዳን ዋድ ሙዛሚል ከተማ መሰብሰባቸውን የገለጹት ኮሊንስ ዋንደሪ የተባለው ኬንያዊ ተንታኝ ናቸው።

“ሰበር ዜና” በሚል “ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የአሸባሪው ህወሓትን ሀሰተኛ መረጃ ለመዘገብ በሱዳን እየተሰባሰቡ ነው ሲል” ኬንያዊው የወንጀል ምርመራና የደህነንት ጉዳዮች ተንታኝ ያስታወቅው በግል የቲውተር ገጹ ላይ ነው።

ኮሊንስ በትዊተር ገጹ ላይ እንዳሰነበበው፤ የአሸባሪው ህወሓት ደጋፊ ሆነው ኢትዮጵያን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙት ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን፣ ሮይተርስ፣ አሶሼትድ ፕሬስ፣ አልጀዚራ፣ ቴሌግራፍ፣ ፍራንስ 24 እና ሌሎች ምእራባዊያን መገናኛ ብዙኃን አሸባሪው ህወሓትን በመደገፍ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለማሰራጨት በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት መሰባሰባቸውን እንዳመለከተ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።

መገናኛ ብዙኃኑ በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ዋድ ሙዛሚል በተባለችው ከተማ መሰባሰባቸውን ያጋለጠው ኬኒያዊው ተንታኝ በሱዳን መንግስት ደጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልጿል።

በቅርቡም ከነዚህ መገናኛ ብዙኃን መካከል አብዛኛዎቹ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሓን ባለስልጣን ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣ የኢትዮጵያን እውነታ አዛብተው በመዘገብ፣ ሚዛናዊና ሙያዊ ያልሆነ መረጃ በማሰራጨት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ይታወቃል። እነዚህ መገናኛ ብዙኃ ከስህተታቸው የማይታረሙ ከሆነም በኢትዮጵያ የመዘገብ ፍቃዳቸው እንደሚሰረዝ ማሰጠንቀቂያ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

እነሱኑ በመተማመን ይመስላል በሳምንቱ መጀመሪያ አዲስ መረጃ እንደሚሰማ ከወዲሁ እየተገለጸ ነው። አንዳንዶችም ከወዲሁ ዘመቻውን ጀምረዋል። በሸዋ ሮቢት ከከሚሴ ሲመታ የተበተነ ሰራዊት እየዘረፈ በየገተሩ ሲሯሯጥ ከተሞች ተያዙ በሚል ሕዝብ እንዲሰደድ እየቀሰቀሱ ነው። መንግስት ሕዝብ እየጨረሰ እንደሆነም እያመለከቱ ነው። አገር ወዳድ የሆኑ ዜጎች በበኩላቸው የህንን ለማክሸፍ የበኩላቸውን እያደረጉ ነው።


Exit mobile version