ETHIO12.COM

” ለቀጣይ 3 ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው ” – የአ/አ ከተማ አስተዳደር

May be an image of text

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከተከራየበት ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ ማተላለፉ ይታወሳል፡፡

አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ ” ይህ ያለንበት ወቅት አገርን ከተጋረጠባት የህልዉና አደጋ የማዳን በመሆኑ ውሳኔውን ለቀጣይ ሶስት ወራት ባለበት እንዲጸና ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ” ብሏል።

በመሆኑም ከዛሬ ሕዳር 17 / 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።


Exit mobile version