Site icon ETHIO12.COM

በኮምቦልቻ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ፤ ከደረቅ ወደብ 800 በላይ ኮንቴነር ሙሉ ዕቃ ተዘርፏል፤ የመንግስት ቀጣይ እርምጃ ይጠበቃል

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ስፍራው ያልሆነውን የአማራና የአፋር ክልልን ከወረረ ብሁዋላ ፈጽሟቸዋል የተባሉ ወንጀሎች እያደር ይፋ እየሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል “ከፍተኛ ወንጀሎች ተፈጽመዋል መርማሪ አሰማርተናል” ብለዋል። ዛሬ በዋላታ ቲቪ መረጃ የሰጡት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ የጅምላ መቃብሮች መገነታቸውን አመልክተዋል። ትህነግ በበኩሉ የስም ማጥፋት እንደተካሄደብት ተቅሶ ” በገባንበት ሁሉ አቀባበል ያደረጉልን፣ የህክምና እርዳታ የሰጠናቸው እናቶች ምስክሮቻችን ናቸው” ሲል መግለጫ አውጥቷል። ዜጎች በማህበራዊ ገጾቻቸው የመንግስትን እርምጃ እንደሚተብቁ እያስታወቁ ነው።

የተለያዩ ከተሞች ነጻ መውጣታቸውን ተከትሎ ይፋ የሆኑ የምስል መረጃዎች እንዳሳዩት ህዝቡ የኢትዮጵያ ሃይሎችን ዳግም መመለስ ” ከዳግም መወለድ” ጋር አነጻጽረው ሲነገሩ፣ ደስታቸው በእልልታና ጭፈራ ሲገልጹ ለማየት ተችሏል። በደሴና በኮምቦልቻ የታየውን ይህ ስሜት በአንድ ወራ ጊዜው ውስጥ “የትህነግ ወራሪ ሃይል ያሳደረባቸው መን ይሆን?” በማለት ሲጠይቁ የነበሩ በርካታ ናቸው።

“ወራሪ ኃይል በከተማዋ ዘረፋ ፈፅሟል። የማይፈልገውን ደግሞ በቻለው አቅም አውድሟል። የሽብር ቡድኑ በዘረፋቸው ተቋማት ግቢ ውስጥም ጅምላ መቃብር ተገኝቷል” ሲሉ የተሰሙት ከንቲባው ናቸው።

የኮምቦልቻ ምክትል ከንቲባ አህመድ የሱፍ “በከተማችን የተለያዩ ቦታዎች በርካታ ንፁሃን ሰዎች በግፍ ተረሽነዋል። ደብዛቸውም ጠፍቷል” ያሉ ሲሆን “በከተማ የተለያዩ ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የጅምላ መቃብር ተገኝተዋል” ሲሉ ዋልታ አሰምቷቸዋል። “ዝርዝሩን መንግሥት አጥንቶ ለከተማው ማኅበረሰብም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገለፅ ይሆናል” ብለዋል።

ዋልታ ቴሌቪዥን በኮምቦልቻ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የጅምላ መቃብር ማየቱን፣ ለቀብር መቆፈሪያና አፈር መመለሻ አገልግሎት የቆመ ኤክስከባተርን መኖሩን፣ ለጅምላ መቃብር ተቆፍሮ የተዘጋጀ ጉድጓድንም ጭምር ማየቱን መስክሯል።

እስካሁን ባለው ሂደት የጅምላ መቃብሮቹ በኮምቦልቻ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ፣ በቃሉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅና የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚገኙ የአይን እማኞች ለዋልታ አስታውቀዋል። “ወራሪ ኃይሉ በኢንደስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በቆየበት አንድ ወር ከአንድ ሳምንት ተቋማትን አውድሟል፤ ዘረፋ ፈፅሟል፤ ሴቶችን ደፍሯል ንፁሃንን ገድሏል” ሲል ዋልታ እማኞችን ጠቅሶ አመልክቷል።

በከተማዋ የሚገኘውን የደረቅ ወደብ ተርማሚናል ከ800 በላይ ኮንቴነር ሙሉ ዕቃ ጭኖ ወስዷል። በከተማዋ ከሚገኘው በተለምዶ ጢጣ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ባለ የነዳጅ ማጠራቀሚያ በየቀኑ በቦቲ ጭኖ ይወሰድ እንደነበር የአይን እማኞች ለዋልታ ተናግረዋል። የኮምቦልቻ ማረሚያ ቤትን ሙሉ ለሙሉ በማቃጠል ማውደሙምም ታውቋል።

በየዕለቱ በሚሰሙት ዜና ቁጣቸው እየበረከተ የመጣ ወገኖች መንግስት በቀጣይ የሚወስደውን እርምጃ እንደሚተብቁ በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው እየጻፉ ነው። አንዳንድ ባለስልጣናትም የከረረ መልዕክት እያስተላለፉ ነው። “እታገለለታለሁ የሚለውን ሕዝቡን ቆሞ አብሮ እንዳዘረፈ እየተመሰከረበት ያለው ሸኔ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ እየደረሰበት ያለውን ውግዘት ለማቃለል ከትህነግ ጋር ጸብ መግባታቸው እየተሰማ ቢሆንም በሁለቱም ላይ እርምጃ እንዲጠናከር ዜጎች እየጠየቁ ነው። መንግስት “ሁለተኛ” ስላለው ዘመቻ እስካሁን የተነፈሰው ነገር የለም። ይህ ሁሉ ሲሆን የውጭ ሚዲያዎችና ታላላቅ የሚባሉት አገራት ምንም አላሉም። የዘገቡ ቢኖሩም በደረሰው ጥፋት ደረጃ እንዳልሆነ መንግስት ማስታወቁ፣ ይህም የጫናውና ኢትዮጵያ እንድትወደም የሚደረገው ሴራ አንዱ አካል መሆኑንን ማስታወቁ አይዘነጋም።

Exit mobile version