በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር የተጠረጠሩ 387 ሰዎች ተያዙ፤ ዜግነታቸው ይፋ አልሆነም

በከፍተኛ የህገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ናቸው የተባሉ 387 ዓለም ዓቀፍ ተጠርታሪዎችን መያዟን የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ አስታወቀ ዜናው ህገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ናቸው የተባሉት 387 ተጠርጣሪዎች አገርና ዜግነትን ይፋ አላደረገም። የተጠርጣሪዎቹ ስምና አገር ይፋ ባይሆንም ዜናው በአገር ቤት መነጋገሪያ ሆኗል።

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ቀደም ሲል 521 ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀሎች ይፋ ተደርገው በጥምረት ክትትል ሲደረግባቸው ነበር።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የተሳተፉ 387 ግለሰቦች ከዓለም አቀፍ የሕግ አስከባሪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር  በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመላክቷል፡፡ ምርመራው በቅንጅት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።

በሕገ ወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ4 ቢሊየን ድርሃም በላይ ገንዘብ በመንግስት መወረሱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ም/ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሌ/ጄ ሼክ ሳይፍ ቢን ዛይድ አል ናህያን ሕገ ወጦችን ለመቆጣጠር የተወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል፡፡

እርምጃው  የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነትከማስጠበቅ ባለፈ በእድገት ጎዳና ላይ የጀመረችውን ጉዞ ለማስቀጥ ል ሚናው ከፍተኛ ነው ማለታቸውን  ገልፍ ቱ  ዴይ  ዘግቧል፡፡

ምንም እንኳን የተጠርጣሪዎቹ ስምና ዜግነት ይፋ ባይሆንም ዜናው በአገር ውስጥ መነጋገሪያ ሆኗል። በርካታ በሙስና ወንጀል የሚጠረጠሩና ከውጭ ገንዘብ ምንዛሬና ኤሊሲ ጋር በተያያዘ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኢመሬትስ ስለሚንቀሳቀሱ፣ መንግስትም ከኢምሬትስ መንግስት ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ስላለው ዜናው ምን አስከትሎ ይመጣ ይሆን የሚል ጉጉትም አሳድሯል።


See also  በኦሮሚያል "የማንወሻሸው ነገር ..." ብ.ጄ ሃይሉ ጎንፋ

Leave a Reply