Site icon ETHIO12.COM

” የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትበህግ ኢትዮጵያ እስካልተስማማች ድረስ ወደ ሀገር የመግባት መብት የላቸውም “

የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በ08/04/2014 ዓ/ም በአብላጫ ድምፅ ያሳለፈውን ውሳኔ (ዓለም አቀፍ የመርማሪ ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ) ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ፤ እንደማታስፈፅም፤ የትኛውም አይነት ትብብር እንደማታደርግ ማሳወቋ ይታወሳል።

የተመርማሪ ሀገር ፍቃድ በሌለበት የመርማሪ ቡድኑ ዕጣ ምን ሊሆን ይችላል ? ኢትዮጵያ ተገዳ መርማሪዎችን የምታስገናግድበት አሰራር ወይም ዓለም አቀፍ ህግ አለ ?

በዚህ ጉዳይ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት ዶክተር አደም ካሴ (በተለይ በአፍሪካ የህግ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ) ተከታዩን ብለዋል ፦

” በዓለም አቀፍ ህግ ይሄን ኮሚሽን በሚመለከት አንድ ሀገር ውስጥ ሊገባ የሚችለው / በሀገሪቱ ገብቶ ሊመረምር የሚችለው በሀገሪቱ ፍቃድ ከተሰጠው ብቻ ነው።

ኢትዮጵያን ሊያስገድዳት የሚችል ስርዓት የለም። ምንም እንኳን የህግ ስርዓት ባይኖርም በፖለቲካ ደረጃ ጫና ሊያመጣ የሚችል ፤ ምን የምትደብቁት ነገር አለ ? እየተባለ ፖለቲካዊ ጫናዎችን ሊያመጣብን ይችላል።

በህግ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት እስካልተስማማ ድረስ ወደ ሀገር የመግባት መብት የላቸውም።

ሌላው ጉዳይ በአጠቃላይ በዓለም ደረጃ ከውሳኔ ሰጪ አካላት በተጨማሪ እነዙህ ውሳኔ አካላትን እየተጠቀሙ አንዳንድ ሀገራት እነሱ የሚደግፉትን አቋም ለማራመድ ይጠቀሙበታል።

በተለይ አሜሪካ እና ምዕራባውያን ኢትዮጵያ ይሄን ቡድን የማታስገባ ከሆነ አንዳንድ ጫናዎች ለማስረግ ለምሳሌ ማዕቀቦችን ለመጫን እና ግፉቶችን ለማድረግ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ኢትዮጵያ በህግ ደረጃ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ የማስገባት ግዴታ ባይኖርባትም በተመድም ከዛም አልፎ ውሳኔውን የሚደግፉ ሀገራት ምዕራባውያን ሀገራትም ያንን ተጠቅመው ጫና ሊያደርጉ ይችላሉ።

ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ አይገቡም ማለት ምርመራውን ማድረግ አይችሉም ማለት አይደለም። ምርመራውን ማካሄድ ይችላሉ፤ ይቀጥላሉ በስልክም በሌላም መንገድ አካሂደው አለ የሚሉትን መረጃ ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ። “

Exit mobile version